አቤት ምህረትህ (Abet Mihretih) - በረከት ተስፋዬ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
በረከት ተስፋዬ
(Bereket Tesfaye)

Lyrics.jpg


(3)

መምህሩ
(Memheru)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2015/2023)
ቁጥር (Track):

(3)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የበረከት ተስፋዬ ፡ አልበሞች
(Albums by Bereket Tesfaye)

አቤት ምህረትህ እንዴት ታላቅ ነው
መለኪያ የለው መስፈሪያ የለው እንዴት ታላቅ ነው እንደምን ታላቅ ነው
ያንት ምህረት ከማን ጋር ይስተያይ
ከፈጠርከው ፍጥረት ከምድር ወይ ሰማይ
የሚስተካከልህ ማን አለ በውኑ
አባቴ ምህረትህ ያክላል አንተኑ

  መለኪያ የለው መስፈሪያ የለው እንዴት ታላቅ (2X)
ሳይታዘዝ ጠላት እጅ ገብቶ
ሳምሶን ወደቀ ከመስመር ወጥቶ
ግን ምህረት ለምኖ መቼ አፈረ
የራሱ ፀጉር ማደግ ጀመረ
በህይወት ከሰራው በሞቱ ባሰ
ለዛ ኪዳን ሰው ምህረት ደረሰ
አንድ ዕድል ብቻ ባይለምንህ
ይኖር ነበረ በቸርነትህ
እንዴት እንዴት እንዴት ታላቅ ነው (2X) እንዴት ኧረ እንዴት
እንዴት እንዴት እንዴት ታላቅ ነው (2X) እንዴት ያንተ ምህረት

  አቤት ምህረትህ...
ብትጨምርለት አስራ አምስት ዓመት
ተዝቆ በማያልቅ ከሰፊ ምህረት
ከኖረበት ዕድሜ ከምህረትህ ወስዶ
አንተን ሳያከብር ጨረሰው በባዶ
እኔንም ገብቶኛል የቃልህ ዕውነት
ለካ ምዘምረው ባንተ ምህረት
መሃሪነትህን እዘምረዋለሁ
በጉልበቴ ሳይሆን በምህረት እኖራለሁ

  እንዴት...
  መለኪያ የለው...