From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
አዝ:- የፍቅር ፡ አምላክ ፡ የሁሉም (፫x)
ደስ ፡ ደስ ፡ ይለኛል
ሥሙን ፡ ስጠራው ፡ የመድኃኒዓለም (፪x)
መድሃኒዓለም ፡ ለዘለዓለም ፡ አይጠገብም ፡ (አሃ) (፪x)
መድሃኒዓለም ፡ አይጠገብም
የእኔ ፡ ኢየሱስ ፡ ዘለዓለም ፡ ንገሥ (፪x)
አሃሃ ፡ ኢየሱስ (፪x) ፡ ኢየሱስ ፡ የምለው
ምህረት ፡ ተደርጐልኝ ፡ ቆሜ ፡ መሄዴ ፡ ነው
ሞኝ ፡ ሆኜ ፡ አይደለም ፡ ወይም ፡ ተታልዬ
ኢየሱስ ፡ የምለው ፡ ሁሉን ፡ ነገር ፡ ጥዬ
ገብቶብኝ ፡ ነው ፡ እንጂ ፡ ታላቁ ፡ ፍቅር
ደቀ ፡ መዝሙር ፡ ሆንኩኝ ፡ ሳላንገራግር
አሸንፎኝ ፡ በፍቅር ፡ አደረገኝ ፡ ደቀ ፡ መዝሙር (፪x)
ከፍቶልኝ ፡ ትልቁን ፡ በር ፡ አደረገኝ ፡ ደቀ ፡ መዝሙር(፪x)
አሃሃ ፡ የድሃ ፡ አደግ ፡ አባት
የመበለት ፡ ዳኛ
ቅንነት ፡ ያለበት ፡ ሁልጊዜ ፡ እውነተኛ
ቢፈለግ ፡ ቢፈለግ ፡ ዓለምም ፡ ቢዞር
አንድም ፡ አይገኝም ፡ እንደእግዚአብሄር
የምስኪን ፡ ጓደኛ ፡ መልካሙ ፡ እረኛ ፡ ኢየሱስ ፡ አለልኛ
ታማኝ ፡ ባልንጀራ ፡ ኢየሱስ ፡ አለልኛ
የምስኪን ፡ ጓደኛ ፡ መልካሙ ፡ እረኛ ፡ ኢየሱስ ፡ አለልኛ
የድሃ ፡ አደግ ፡ አባት ፡ የመበለት ፡ ዳኛ ፡ ኢየሱስ ፡ አለልኛ
የምስኪን ፡ ጓደኛ ፡ መልካሙ ፡ እረኛ
ታማኝ ፡ ባልንጀራ ፡ ኢየሱስ ፡ አለልኛ
የድሃ ፡ አደግ ፡ አባት ፡ የመበለት ፡ ዳኛ
ቅንነት ፡ ያለበት ፡ ሁልጊዜ ፡ እውነተኛ
አዝ:- የፍቅር ፡ አምላክ ፡ የሁሉም (፫x)
ደስ ፡ ደስ ፡ ይለኛል
ሥሙን ፡ ስጠራው ፡ የመድኃኒዓለም (፪x)
መድሃኒዓለም ፡ ለዘለዓለም ፡ አይጠገብም ፡ (አሃ) (፪x)
መድሃኒዓለም ፡ አይጠገብም
የእኔ ፡ ኢየሱስ ፡ ዘለዓለም ፡ ንገሥ (፪x)
አሃሃ ፡ ቸሩ ፡ መድሃኒዓለም ፡ የዓለም ፡ መድሃኒት
ለእኛ ፡ የደረሰ ፡ በአስጨናቂው ፡ ሌሊት
ሥሙ ፡ ይታወጅ ፡ በአገሬ ፡ ላይ
የኢትዮጵያ ፡ አምላክ ፡ እርሱ ፡ አይደለም ፡ ወይ
ዘንዶውንም ፡ ወጋ ፡ ረሃብን ፡ ቆራረጠ
ለሃገሬ ፡ ልጆች ፡ ምግባቸውን ፡ ሰጠ
የኢትዮጵያ ፡ አምላክ (፪x) ፡ ሥምህ ፡ ይባረክ (፪x)
የኢትዮጵያ ፡ አምላክ ፡ ሥምህ ፡ ይባረክ
የእኛ ፡ አምላክ ፡ ሥምህ ፡ ይባረክ
የኢትዮጵያ ፡ አምላክ ፡ ሥምህ ፡ ይባረክ
የእስራኤል ፡ አምላክ ፡ ሥምህ ፡ ይባረክ
|