ሊቀ ፡ ካህኔ (Liqe Kahenie) - በረከት ፡ ተስፋዬ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
በረከት ፡ ተስፋዬ
(Bereket Tesfaye)

Bereket Tesfaye 1.jpeg


(1)

ሊቀ ፡ ካህኔ
(Liqe Kahenie)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ (2007)
ቁጥር (Track):

(3)

ርዝመት (Len.): 5:05
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የበረከት ፡ ተስፋዬ ፡ አልበሞች
(Albums by Bereket Tesfaye)

ስደክም ፡ የሚያበረታኝ
በውድቀቴ ፡ የማይስቅብኝ
በፍቅር ፡ ዓይኖቹ ፡ የሚያየኝ
ደጉ ፡ ሊቀ ፡ ካህን ፡ አለኝ (፪x)

አዝ:- ሊቀ ፡ ካህኔ ፡ ኢየሱሴ (፪x)
ጠበቃዬ ፡ ኢየሱሴ
አለልኝ ፡ በሰማይ ፡ ለነፍሴ (፪x)

ታማኙ ፡ የነፍሴ ፡ ጠባቂ
ኢየሱስ ፡ ለእኔ ፡ አዋቂ
ዳኛዬ ፡ ቅኑ ፡ ፈራጄ
ኢየሱስ ፡ እርሱስ ፡ ወዳጄ

የልጅነት ፡ አባት ፡ የሆነኝ
እንዳልወድቅ ፡ የቆመልኝ
ካህኔ ፡ ጠባቂ ፡ የነፍሴ
ይገባሃል ፡ አምልኮ ፡ ውዳሴ

የልጅነት ፡ አባት ፡ የሆነኝ
እንዳልወድቅ ፡ የቆመልኝ
ካህኔ ፡ የነፍሴ ፡ ጠባቂ
ኢየሱስ ፡ ለእኔ ፡ አዋቂ

ታማኙ ፡ የነፍሴ ፡ ጠባቂ
ኢየሱስ ፡ ለእኔ ፡ አዋቂ
ዳኛዬ ፡ ቅኑ ፡ ፈራጄ
ኢየሱስ ፡ እርሱስ ፡ ወዳጄ

ጉድ ፡ አሉ ፡ የሚያውቁኝ ፡ በሙሉ
በመቆሜ ፡ ሁሉም ፡ ተገረሙ
እኔ ፡ ግን ፡ እንደዚህ ፡ እላለሁ
መቆሜ ፡ ከእርሱ ፡ የተነሳ ፡ ነው (፪x)

አዝ:- ሊቀ ፡ ካህኔ ፡ ኢየሱሴ (፪x)
ጠበቃዬ ፡ ኢየሱሴ
አለልኝ ፡ በሰማይ ፡ ለነፍሴ (፪x)