From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
በዓለም ፡ ፍቅር ፡ እንዳልነደፍ
ከሚጠፉት ፡ ጋር ፡ እንዳልሰለፍ
አረማመዴን ፡ አቅናውና
የራስህ ፡ አድርገኝ ፡ ቀይረኝና
ከሚጠፉት ፡ እንዳልሆን ፡ ጠብቀኝ::
ጌታ ፡ ሆይ ፡ ምህረትህን ፡ አብዛልኝ (፪x)
አንተ ፡ የሌለህበት
የዓለም ፡ ዝና ፡ የዓለም ፡ ዕውቀት
ኢሄ ፡ ሁሉ ፡ ከንቱ ፡ ነዉ
ንፋስን ፡ እንደመከተል ፡ ነው
ከሚጠፉት ፡ እንዳልሆን ፡ ጠብቀኝ::
ጌታ ፡ ሆይ ፡ ምህረትህን ፡ አብዛልኝ (፪x)
በአንደበቴ ፡ እንዳልረክስ
ወንድሜንም ፡ እንዳልተነኩስ
አቤቱ ፡ ማስተዋልን ፡ ስጠኝ
መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ና ፡ አስተምረኝ
ከሚጠፉት ፡ እንዳልሆን ፡ ጠብቀኝ::
ጌታ ፡ ሆይ ፡ ምህረትህን ፡ አብዛልኝ (፪x)
ዓይኔን ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ እንዳቀና
መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ናልኝና
ፈውሰኝ ፡ ቀድሰኝ
መጠቀሚያ ፡ ገንዘብህ ፡ አድርገኝ
ከሚጠፉት ፡ እንዳልሆን ፡ ጠብቀኝ::
ጌታ ፡ ሆይ ፡ ምህረትህን ፡ አብዛልኝ (፪x)
|