ጌታዬ ፡ ጌታዬ (Gietayie Gietayie) - በረከት ፡ ተስፋዬ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
በረከት ፡ ተስፋዬ
(Bereket Tesfaye)

Bereket Tesfaye 1.jpeg


(1)

ሊቀ ፡ ካህኔ
(Liqe Kahenie)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ (2007)
ቁጥር (Track):

፲ ፫ (13)

ርዝመት (Len.): 5:21
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የበረከት ፡ ተስፋዬ ፡ አልበሞች
(Albums by Bereket Tesfaye)

ብቻዬን ፡ ቁጭ ፡ ብዬ ፡ አዝኜ ፡ በቤቴ
በጣም ፡ እያመመኝ ፡ ይሄው ፡ ስብራቴ
በድንገት ፡ ኢየሱስ ፡ ደረሰልኝ
ሰባራውን ፡ ጠጋኝ ፡ እውነተኛ ፡ ዳኛ

የደካሞች ፡ አሳራፊ
ኢየሱስ ፡ አለ ፡ ነፍሴ ፡ እረፊ
ሸክም ፡ ከብዶበት ፡ የሚንገላታ
ወደዚህ ፡ ጌታ ፡ መጥቶ ፡ ይበርታ
ዓይኔን ፡ አንስቼ ፡ ከሰው ፡ ላይ
ሀዘኔን ፡ ረሳሁ ፡ ኢየሱስን ፡ ሳይ

አዝ:- ጌታዬ ፡ ጌታዬ ፡ ከሞት ፡ መዳኛዬ
ኢየሱስ ፡ ጌታዬ ፡ የዓይኔ ፡ ማረፊያዬ

የፈተና ፡ መዓት ፡ በላዬ ፡ ቢፈስ
ፀሎቴም ፡ በሙሉ ፡ ባይመለስ
ዝቅ ፡ ዝቅ ፡ እላለሁ ፡ ሌላ ፡ አያምረኝም
ቤዛዬን ፡ ኢየሱስ ፡ በፍፁም ፡ አልክድም (፪x)

አዝ:- ጌታዬ ፡ ጌታዬ ፡ የዓይኔ ፡ ማረፊያዬ
ኢየሱስ ፡ ጌታዬ ፡ ከሞት ፡ መዳኛዬ
ጌታዬ ፡ ጌታዬ ፡ ከሞት ፡ መዳኛዬ
ኢየሱስ ፡ ጌታዬ ፡ የዓይኔ ፡ ማረፊያዬ

ኃጢአተኛ ፡ ሳለሁ ፡ ሰዎች ፡ ሲገፉኝ
የናዝሬቱ ፡ ኢየሱስ ፡ አይቶ ፡ ራራልኝ
እንደ ፡ ኃጢአቴ ፡ ያልፈረደብኝ
የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ እርሱ ፡ ለእኔ ፡ አዘነልኝ

አዝ:- ጌታዬ ፡ ጌታዬ ፡ የዓይኔ ፡ ማረፊያዬ
ኢየሱስ ፡ ጌታዬ ፡ ከሞት ፡ መዳኛዬ
ጌታዬ ፡ ጌታዬ ፡ ከሞት ፡ መዳኛዬ
ኢየሱስ ፡ ጌታዬ ፡ የዓይኔ ፡ ማረፊያዬ

የደካሞች ፡ አሳራፊ
ኢየሱስ ፡ አለ ፡ ነፍሴ ፡ እረፊ
ሸክም ፡ ከብዶበት ፡ የሚንገላታ
ወደዚህ ፡ ጌታ ፡ መጥቶ ፡ ይበርታ
ዓይኔን ፡ አንስቼ ፡ ከሰው ፡ ላይ
ሀዘኔን ፡ ረሳሁ ፡ ኢየሱስን ፡ ሳይ

አዝ:- ጌታዬ ፡ ጌታዬ ፡ ከሞት ፡ መዳኛዬ
ኢየሱስ ፡ ጌታዬ ፡ የዓይኔ ፡ ማረፊያዬ