እግዚአብሔር ፡ መልካም ፡ ነው (Egziabhier Melkam New) - በረከት ፡ ተስፋዬ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
በረከት ፡ ተስፋዬ
(Bereket Tesfaye)

Bereket Tesfaye 1.jpeg


(1)

ሊቀ ፡ ካህኔ
(Liqe Kahenie)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ (2007)
ቁጥር (Track):

(1)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የበረከት ፡ ተስፋዬ ፡ አልበሞች
(Albums by Bereket Tesfaye)

በሕይወቴ ፡ ያለፈውን ፡ ዞር ፡ ብይ ፡ ሳየው ፡ ስመለከተው
የእኔ ፡ ጉልበት ፡ ሳይሆን ፡ እዚህ ፡ ያደረሰኝ ፡ መልካምነቱ ፡ ነው
የእኔ ፡ ብርታት ፡ ሳይሆን ፡ እዚህ ፡ ያደረሰኝ ፡ ኧረ ፡ እርሱ ፡ ጌታ ፡ ነው

አዝእግዚአብሔር ፡ መልካም ፡ ነው (፪x)
የሚመስለው ፡ ማነው
በመልካምነቱ ፡ በመልካምነቱ ፡ ታጋሽ ፡ ርህሩህነቱ
ነገሬ ፡ የሰመረው (፫x)
ከኢየሱስ ፡ የተነሳ ፡ ነው (፪x)
ከኢየሱስ ፡ የተነሳ ፡ ነው (፬x)

የእራሴ ፡ አስተዋፅዖ ፡ አንድም ፡ የሌለበት
ያልደከምኩበት ፡ እዚህ ፡ ለመድረሴ ፡
ምክንያቱ ፡ አንድ ፡ ነው ፡ እግዚአብሄር ፡ መልካም ፡ ነው (፪x)

አዝእግዚአብሔር ፡ መልካም ፡ ነው (፪x)
የሚመስለው ፡ ማነው
በመልካምነቱ ፡ በመልካምነቱ ፡ ታጋሽ ፡ ርህሩህነቱ
ነገሬ ፡ የሰመረው (፫x)
ከኢየሱስ ፡ የተነሳ ፡ ነው (፪x)
ከኢየሱስ ፡ የተነሳ ፡ ነው (፬x)

በምድረ ፡ በዳ ፡ ላይ ፡ አንድ ፡ ነገር ፡ ሳይኖር
ምንጭን ፡ አፈለቀ ፡ ጌታ ፡ በተዓምር
የምድረ ፡ በዳዉ ፡ ሃሩር ፡ ሳያገኘኝ
የነ ፡ ሙሴ ፡ አምላክ ፡ ተጠነቀቀልኝ

ወጥመድ ፡ ተሰበረ ፡ ወጥመድ ፡ ተሰበረ
ጌትዬ ፡ ከበረ
ወጥመዱን ፡ ሲሰብረው ፡ ወጥመዱን ፡ ሲሰብረው
ባይኔ ፡ አይቻለሁ

በሕይወቴ ፡ ያለፈውን ፡ ዞር ፡ ብይ ፡ ሳየው ፡ ስመለከተው
የእኔ ፡ ጉልበት ፡ ሳይሆን ፡ እዚህ ፡ ያደረሰኝ ፡ መልካምነቱ ፡ ነው
የእኔ ፡ ብርታት ፡ ሳይሆን ፡ እዚህ ፡ ያደረሰኝ ፡ ኧረ ፡ እሱ ፡ ጌታ ፡ ነው

አዝእግዚአብሔር ፡ መልካም ፡ ነው (፪x)
የሚመስለው ፡ ማነው
በመልካምነቱ ፡ በመልካምነቱ ፡ ታጋሽ ፡ ርህሩህነቱ
ነገሬ ፡ የሰመረው (፫x)
ከኢየሱስ ፡ የተነሳ ፡ ነው (፪x)
ከኢየሱስ ፡ የተነሳ ፡ ነው (፬x)