ዕድሜዬን (Edmieyien) - በረከት ፡ ተስፋዬ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
በረከት ፡ ተስፋዬ
(Bereket Tesfaye)

Bereket Tesfaye 1.jpeg


(1)

ሊቀ ፡ ካህኔ
(Liqe Kahenie)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ (2007)
ቁጥር (Track):

(5)

ርዝመት (Len.): 5:08
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የበረከት ፡ ተስፋዬ ፡ አልበሞች
(Albums by Bereket Tesfaye)

ዕድሜዬን ፡ በሙሉ ፡ ብሰጠው ፡ አይቆጨኝም
በመስቀል ፡ ደሙን ፡ ላፈሰሰልኝ
ሰው ፡ ሁሉ ፡ ንጹህ ፡ ሆኖ ፡ እኔ ፡ ግን ፡ ብቆሽሽ
በምድር ፡ ላይ ፡ እኔ ፡ ብቻ ፡ በኀጢአት ፡ ብበላሽ
መሞት ፡ የሚገባኝ ፡ እኔ ፡ ብቻ ፡ ብሆን
ኢየሱስ ፡ ለብቻዬ ፡ ይመጣልኝ ፡ ነበር

አዝ:- እንደ ፡ ኢየሱስ ፡ በምድር ፡ ላይ
ፈልጌ ፡ አጣሁ ፡ እርሱን ፡ መሳይ
ኦ ፡ ስለዚህ ፡ እኔ ፡ አመልካለሁ
ቀሪ ፡ ዘመኔ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው

ክፉ ፡ አመሌን ፡ አይቶ ፡ ከቶ ፡ ያልሰለቸው
አስቸጋሪ ፡ ባሕሪዬ ፡ ልቡን ፡ ያላራደው
በፍቅሩ ፡ አሸነፈኝ ፡ የራሱ ፡ አደረገኝ
የማይገባኝን ፡ ክብር ፡ አለበሰኝ

አዝ:- እንደ ፡ ኢየሱስ ፡ በምድር ፡ ላይ
ፈልጌ ፡ አጣሁ ፡ እርሱን ፡ መሳይ
ኦ ፡ ስለዚህ ፡ እኔ ፡ አመልካለሁ
ቀሪ ፡ ዘመኔ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው

ዕድሜዬን ፡ በሙሉ ፡ ብሰጠው ፡ አይቆጨኝም
በመስቀል ፡ ላይ ፡ ሞቶ ፡ ራሱን ፡ ለሰጠኝ
አዋርዳለሁኝ ፡ ሁለንተናዬን ፡ ለእርሱ
ዳግም ፡ ወዶኛልና ፡ ኢየሱስ ፡ ንጉሡ

የፍቅር ፡ ትርጉም ፡ የገባዉ
ኧረ ፡ ማነው ፡ ሚገልጸዉ
የአፍቃሩ ፡ ትርጉም ፡ ማነው ፡ እርሱ
ኢየሱስ ፡ ያልራራ ፡ ለነፍሱ (፪x)

አዝ:- እንደ ፡ ኢየሱስ ፡ በምድር ፡ ላይ
ፈልጌ ፡ አጣሁ ፡ እርሱን ፡ መሳይ
ኦ ፡ ስለዚህ ፡ እኔ ፡ አመልካለሁ
ቀሪ ፡ ዘመኔ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው