From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ለእኔ ፡ ቀኑ ፡ ጨልሞ ፡ መስማት ፡ እንጂ ፡ ማየት ፡ አልችል
ጥዋት ፡ ልለምን ፡ የወጣሁ ፡ መሽቶ ፡ በሰው ፡ ነው ፡ ምገባው
ትንሽ ፡ ትልቅ ፡ መሪዬ ፡ የሰው ፡ ፍቃድ ፡ ማደሪያዬ
የእድሜዬን ፡ ግማሽ ፡ ቆጠርኩ ፡ ጨለማውን ፡ ለመድኩ
መጣ ፡ ኢየሱስ
ይሄ ፡ የአለም ፡ ብርሃን
ዓይኖቼን ፡ ከፈተ ፡ በእውርነቴ ፡ ሃገር
ታሪኬ ፡ ተለወጠ (፪x)
የዳዊት ፡ ልጅ ፡ ማረኝ ፡ ብዬ ፡ ተከፈተ ፡ ብርሃኔ
መልካምነቱን ፡ አየሁት ፡ በዚህች ፡ በአጭሯ ፡ ዘመኔ
ተጥዬ ፡ የነበርኩ ፡ ያምስኪኑ ፡ እኔ ፡ ነኝ
መንገደኛ ፡ የማያየኝ ፡ አሳዛኝ ፡ ሰው ፡ ነበርኩኝ
በሀጥያቱ ፡ ወደቀ ፡ በእግዚአብሔር ፡ ደቀቀ
ብለው ፡ ሰዎች ፡ ፈርዱ ፡ ስብራቴን ፡ ሳይረዱ
ደጉ ፡ ጌታ ፡ ከሰማይ ፡ አየኝ
ከውድቀቴ ፡ አነሳኝ ፡ ቁስሌን ፡ ፈውሶ
አከበረኝ ፡ መልሶ (፪x)
በታምራት ፡ የሚያኖረኝ ፡ አምላክ ፡ አለኝ ፡ የሚያስብልኝ
የመቆሜ ፡ ምክንያቱ ፡ የእግዚአብሔር ፡ ምህረቱ
ባልጋዬ ፡ ላይ ፡ ተኝቼ ፡ ለአመታት ፡ ሸትቼ
መልዐኩ ፡ ሲያናውጠው ፡ ማን ፡ ሊከተኝ ፡ ወደ ፡ ውሃው
ዘመድ ፡ አዝማድ ፡ የለኝ ፡ እኔ ፡ የምለው ፡ ሚረዳኝ
ቀርቦ ፡ ችግሬን ፡ አየና ፡ ተራመድ ፡ ሂድ ፡ ተነሳና
ያለው ፡ ጌታ ፡ ለካ ፡ ዘመዴ ፡ ነው ፡ ስለ ፡ እኔ ፡ የሚሰማው
ሽባነቴን ፡ ሽሮ ፡ አቆመኝ ፡ ቀይሮ ፡(፪x)
በታምራት ፡ የሚያኖረኝ ፡ አምላክ ፡ አለኝ ፡ የሚያስብልኝ
የመቆሜ ፡ ምክንያቱ ፡ የእግዚአብሔር ፡ ምህረቱ
|