አፈታሪክ ፡ አይደለም (Afetarik Aydelem) - በረከት ፡ ተስፋዬ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
በረከት ፡ ተስፋዬ
(Bereket Tesfaye)

Bereket Tesfaye 1.jpeg


(1)

ሊቀ ፡ ካህኔ
(Liqe Kahenie)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ (2007)
ቁጥር (Track):

(7)

ርዝመት (Len.): 4:48
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የበረከት ፡ ተስፋዬ ፡ አልበሞች
(Albums by Bereket Tesfaye)

አፈ ፡ ታሪክ ፡ አይደለ ፡ ወይንም ፡ ተረት
የኢየሱሴ ፡ ኃይልና ፡ ብርታት
ጌታ ፡ አሁንም ፡ በሥራ ፡ ላይ ፡ ነው
የሚያግደው ፡ እስኪ ፡ ማነው

የተፈጥሮ ፡ ሕግ ፡ አያግደው
ጌታችን ፡ ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ነው
የማይበገረው ፡ አንበሳ
ኢየሱስ ፡ ከሞት ፡ ተነሳ

የበላይ ፡ ኢየሱስ ፡ የበላይ (፬x)
አዶናይ ፡ ኢየሱስ ፡ የበላይ (፬x)

ኃያላን ፡ በሞት ፡ ሲሻሩ
አልቻሉም ፡ መቃብር ፡ ቀሩ
ኢየሱስ ፡ ግን ፡ የይሁዳ ፡ አንበሳ
አሸነፈ ፡ ሞትን ፡ ድል ፡ ነሳ

ከፍ ፡ ያለ ፡ በከፍታ ፡ ላይ (፫x)
ኢየሱስ ፡ ገኖ ፡ የሚታይ
ከፍ ፡ ያለ ፡ በከፍታ ፡ ላይ (፫x)
ውድዬ ፡ ገኖ ፡ የሚታይ

የንጋት ፡ ኮከብ ፡ ብርሃን
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ለዘለዓለም ፡ (ነው (፫x))
ፊቱ ፡ እንደ ፡ ፀሐይ ፡ የሚያበራ
የእኔ ፡ ኢየሱስ ፡ ባለ ፡ ግርማ ፡ (ነው (፫x))
ማኅተሙን ፡ በአንዴ ፡ የፈታ
የእኔ ፡ ኢየሱስ ፡ ብቸኛ ፡ ጌታ ፡ (ነው (፫x))

ከፍ ፡ ያለ ፡ በከፍታ ፡ ላይ (፫x)
ኢየሱስ ፡ ገኖ ፡ የሚታይ
ከፍ ፡ ያለ ፡ በከፍታ ፡ ላይ (፫x)
ውድዬ ፡ ገኖ ፡ የሚታይ

ባሕር ፡ ላይ ፡ የሚራመደው
የቱ ፡ ጀግና ፡ ነው ፡ የሚሞክረው
የእኔ ፡ ኢየሱስ ፡ ውኃ ፡ አይዘው
ይራመዳል ፡ እንደፈለገው

አዶናይ ፡ ኢየሱስ ፡ የበላይ (፰x)

አፈ ፡ ታሪክ ፡ አይደለ ፡ ወይንም ፡ ተረት
የኢየሱሴ ፡ ኃይልና ፡ ብርታት
ጌታ ፡ አሁንም ፡ በሥራ ፡ ላይ ፡ ነው
የሚያግደው ፡ እስኪ ፡ ማነው

የንጋት ፡ ኮከብ ፡ ብርሃን
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ለዘለዓለም ፡ (ነው (፫x))
ፊቱ ፡ እንደ ፡ ፀሐይ ፡ የሚያበራ
የእኔ ፡ ኢየሱስ ፡ ባለ ፡ ግርማ ፡ (ነው (፫x))
ማኅተሙን ፡ በአንዴ ፡ የፈታ
የእኔ ፡ ኢየሱስ ፡ ብቸኛ ፡ ጌታ ፡ (ነው (፫x))

ከፍ ፡ ያለ ፡ በከፍታ ፡ ላይ (፫x)
ኢየሱስ ፡ ገኖ ፡ የሚታይ
ከፍ ፡ ያለ ፡ በከፍታ ፡ ላይ (፫x)
ውድዬ ፡ ገኖ ፡ የሚታይ

የተፈጥሮ ፡ ሕግ ፡ አያግደው
ጌታችን ፡ ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ነው
የማይበገረው ፡ አንበሳ
ኢየሱስ ፡ ከሞት ፡ ተነሳ

ከፍ ፡ ያለ ፡ በከፍታ ፡ ላይ (፫x)
ኢየሱስ ፡ ገኖ ፡ የሚታይ
ከፍ ፡ ያለ ፡ በከፍታ ፡ ላይ (፫x)
ውድዬ ፡ ገኖ ፡ የሚታይ

የንጋት ፡ ኮከብ ፡ ብርሃን
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ለዘለዓለም ፡ (ነው (፫x))
ፊቱ ፡ እንደ ፡ ፀሐይ ፡ የሚያበራ
የእኔ ፡ ኢየሱስ ፡ ባለ ፡ ግርማ ፡ (ነው (፫x))
ማኅተሙን ፡ በአንዴ ፡ የፈታ
የእኔ ፡ ኢየሱስ ፡ ብቸኛ ፡ ጌታ ፡ (ነው (፫x))

የበላይ ፡ ኢየሱስ ፡ የበላይ (፬x)
አዶናይ ፡ ኢየሱስ ፡ የበላይ (፬x)