አለው (Alew) - በረከት ተስፋዬ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
በረከት ተስፋዬ
(Bereket Tesfaye)

Lyrics.jpg


(3)

አልበም
(3)

ዓ.ም. (Year): 2023
ቁጥር (Track):

(1)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የበረከት ተስፋዬ ፡ አልበሞች
(Albums by Bereket Tesfaye)

አለሁ በምህረቱ አለሁ በይቅርታው (እየማረኝ) አለሁ
አለሁ ምህረት አጊንቻለሁ እኔ ምን እሆናለሁ
  አለሁ ሞቴ ተሽሯል አለሁ ምህረቱ ገኗል አለሁ
  አለሁ ህመሜን ወስዷል አለሁ እኔ ምን እሆናለሁ
እነ ሚካኤል እነ ገብርኤል
እነ ሱራፌል እነ ኪሩቤል
በክንፎቻቸው ተከልለውት
ፊቱ ሚቆሙለት አምላክ የሚሉት
በገራፊዎች ፊት ቆመልኝ እሱ ግን ስለ እኔ
ፍቅር ግድ ቢለው ሊያወጣኝ ከኃጢያት ከኩነኔ
ዙፋን የነበረው ከሰማይ ዳዊትን የረዳ
ተንከራተተልኝ ኢየሱስ ከናዝሬት ይሁዳ
ፍቅሩ ፈሰሰ ከምህረት ደጅ
እግዚአብሔር ከሰማይ ሰጠኝ አንድ ልጅ
ኑሮዬን ኑር አለኝ የእኔን ልብሰ ለበሰ
ቆሻሻ ሂወቴን በደሙ ቀደሰ
    አለሁ ሞቴ ተሽሯል...

ይሁን በምትል ቃል ፍጥረትን የሰራ
ጥበብ የሻተውን ጥበብን ያስወራ
አባቶች ሲጠሩት በእሳት የመለሰ
እረኛው ዳዊትን ተናግሮ ያነገሰ
እንደሚታረድ በግ ዝም አለ ስለ እኔ ኢየሱስ
ፍቅርን የኖረ በተግባር የፍቅር ንጉስ
ምድርን ያቆመ በቃሉ ያላንዳች ምሶሶ
እሱ ግን ዝም አለ ሞተልኝ የእኔን ውርደት ለብሶ
  ፍቅሩ ፈሰሰ...
አለሁ ሞቴ ተሽሯል...
አለሁ በምህረቱ አለሁ...

አብ ከላይ ሆኖ ለኔ ራራልኝ አዘነ
ሊያድነኝ ሽቶ አንድ ልጁ ላይ ጨከነ
ፍቅር ልሂድ አለ ታዘዘ ለአባቱ
ክብሩን ትቶ ወርዶ አዳነኝ በሞቱ
ፍቅር እንደ ኢየሱስ የለም (8X)