ሞት ፡ መሻገሪያዬ (Mot Meshageriyayie) - በረከት ፡ ፈቃዱ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
በረከት ፡ ፈቃዱ
(Bereket Fekadu)


(2)

ሞት ፡ መሻገሪያዬ
(Mot Meshageriyayie)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2013)
ቁጥር (Track):

(1)

ርዝመት (Len.): 3:35
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የበረከት ፡ ፈቃዱ ፡ አልበሞች
(Albums by Bereket Fekadu)

ሞት ፡ መሻገሪያዬ
ወደ ፡ ዘላለም ፡ ቤት ፡ ማለፊያዬ
የናፈቁትን ፡ የምወርስበት
አምላኬን ፡ የማገኝበት
የዘላለም ፡ ቤት ፡ መግቢያዬ
ሞት ፡ መሻገሪያዬ (፪x)

የእኔ ፡ ኑሮ ፡ በዚህ ፡ ምድር ፡ ላይ ፡ አያበቃም
ቆይታዬ ፡ መጨረሺያዬ ፡ በዚህ ፡ አይደለም
ይቀጥላል ፡ ከሞት ፡ ወዲያ ፡ በአዲስ ፡ ሕይወት
በዘለዓለም ፡ ቤት ፡ በደስታዬ ፡ ቤት (፪x)

ምኞቴን ፡ አይደለም ፡ የምናገረው
በእርግጥ ፡ የሚሆን ፡ የሚታይ ፡ ነው
በቃሉ ፡ እንደገባልኝ ፡ ቃል ፡ ኪዳን
ከሞት ፡ ወዲያ ፡ ከእርሱ ፡ ጋር ፡ እንደምሆን ፡ ነው (፪x)

ሞትን ፡ ድል ፡ ነስቶልኛል
እንዴት ፡ ውጦ ፡ ያስቀረኛል
ተሻግሯል ፡ አልፏል ፡ ኑሮዬ
አልቀርም ፡ በሞት ፡ ተይዤ
ሞት ፡ ለእኔ ፡ ጥቅሜ ፡ ነው
ሞት ፡ ለእኔ ፡ ክብሬ ፡ ነው (፪x)