አንተ ፡ ግን ፡ ያው ፡ አንተ ፡ ነህ (Ante Gen Yaw Ante Neh) - በረከት ፡ ፈቃዱ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
Broom.png ይህ ፡ ጽሑፍ ፡ ገና ፡ አልተረጋገጠም ። እርማቶች ፡ ሊያስፈልጉት ፡ ይችላል ። ከቻሉ ፡ እርስዎ ፡ ያሻሽሉት
በረከት ፡ ፈቃዱ
(Bereket Fekadu)

Bereket Fekadu 2.jpg


(2)

ሞት ፡ መሻገሪያዬ
(Mot Meshageriyayie)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2013)
ቁጥር (Track):

(2)

ርዝመት (Len.): 6:03
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የበረከት ፡ ፈቃዱ ፡ አልበሞች
(Albums by Bereket Fekadu)

እስከዛሬ እኔ ያየሁት ሃ የተረዳሁት
መልካምነትህን ነዉ የማዉቀው አታውቅም ክፋት
ባለፍኩበት ሁሉ ከኔ ጋር የሆንክ
የልጅነቴ አምላክ እግዚአብሔር
አይኔ ያየው ይሄንን ነው መልካምነትህን ነው
አይኔ ያየው ይሄንን ነው መልካምነትህን

አሃ መንገዴን ሁሉ እየመራኸኝ
ያልተለወጥክብኝ አንተ ብቻ ነህ
አንተ ግን አንተ ነህ አንተ ብቻ ነህ

ሁሉ ፡ ሲለዋወጥ ፡ ኣንተ ፡ ግን ፡ ኣንተ ፡ነህ ኣትለዋወጥም
ነገር ፡ ሲለዋወጥ ፡ ኣንተ ፡ ግን ፡ ኣንተ ፡ነህ ኣትለዋወጥም

በማደርያው ፡ ላይ ፡ ያለኸው ፡ በዙፋኑ ፡ ላይ ፡ ያለኸው ፡ ኣንተ ፡ ግን ፡ ኣንተ ነህ (፪x)

ኣንዴ ፡ ስንወድቅ ፡ ኣንዴ ፡ ስንነሳ ፡
 ያሳለፍነው ፡ ነገር ፡ እስኬ ፡ እንዴ ፡ ይወሳ
በጠራነው ፡ ጊዜ ፡ ለኣፍታም ፡ ሳይዘገይ ፡
እዚ ፡ ያደረሰን ፡ እሱ ፡ ኣይደለም ፡ ወይ

በማደርያው ፡ ላይ ፡ ያለው ፡ በዙፋኑ ፡ ላይ ፡ ያለው ፡ እሱ እንዴት ድንቅ ነው(፪x)

ሁሉ ፡ ሲለዋወጥ ፡ ኣሃ ፡ ኣንተ ፡ ግን ፡ ኣንተ ፡ነህ ኣትለዋወጥም
ነገር ፡ ሲለዋወጥ ፡ ኣሃ ፡ ኣንተ ፡ ግን ፡ ኣንተ ፡ ነህ ኣትለዋወጥም

በማደርያው ፡ ላይ ፡ ያለኸው ፡ በዙፋኑ ፡ ላይ ፡ ያለኸው ፡ ኣንተ ፡ ግን ፡ ኣንተ ነህ (፪x)

ጭንቅ ጥብብ ብሎን ፡ ማን ፡ ኣለልኝ ፡ ስንል
በኛ ፡ ላይ ፡ ምክሩ ፡ በርትቶ ፡ ሲያይል
የተረሳን ፡ መስሎን ፡ ከመከራው ፡ ብዛት ፡
ግን ፡ እሱ ፡ ኣቆመን ፡ እየሆነ ፡ አባት

በማደርያው: ላይ ፡ ያለኸው ፡ በዙፋኑ ፡ ላይ ፡ ያለኸው ፡ ኣንተ ፡ ግን ፡ ኣንተ ነህ (፪x)

ሁሉ ፡ ሲለዋወጥ ፡ ኣሃ ፡ ኣንተ ፡ ግን ፡ ኣንተ ፡ ኣትለዋወጥም
ነገር ፡ ሲለዋወጥ ፡ ኣሃ ፡ ኣንተ ፡ ግን ፡ ኣንተ ፡ ኣትለዋወጥም

በማደርያው ፡ ላይ ፡ ያለው ፡ በዙፋኑ ፡ ላይ ፡ ያለው ፡ እርሱ ፡ እንዴት ድንቅ ነው (፪x)

ከርሱ ፡ ጋር ፡ ስንጎዝ ፡ ባለፉት ፡ ዘመናት ፡
 ስንቴ ፡ ኣሳለፈን ፡ ክፉዎቹን ፡ ቀናት
እጃችንን ፡ ይዞ ፡ በድል ፡ እየመራ ፡
እስከ ፡ ዛሬ ፡ ድረስ ፡ በምረቱ ፡ ኣቆመን

በማደርያው ፡ ላይ ፡ ያለው ፡ በዙፋኑ ፡ ላይ ፡ ያዉ ፡ እርሱ ፡ ድንቅ ነው (፬x)