From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
አዝ፦ የወይኑ ፡ ቦታ ፡ አሄ ፡ እህህም ፡ የወይኑ ፡ ቦታ
አወይ ፡ የወይኑ ፡ ቦታ ፡ አሄ ፡ እህህም ፡ የወይኑ ፡ ቦታ
በአግባብ ፡ ተቆፍሮ ፡ አሄሄ ፡ ድንጋይም ፡ ተለቅሞ
ኦ ፡ ምርጥ ፡ የተባለን ፡ ዘር ፡ ከእርሱ ፡ ዘንዳ
ከእርሱ ፡ ዘንታ ፡ ተክሎ
ኧረ ፡ እኔስ ፡ አልገባኝም ፡ አሄሄ ፡ መራራ ፡ ማፍራቱ
ይህን ፡ ክፉ ፡ ፍሬ ፡ አሃሃም ፡ ለጌታው ፡ መስጠቱ
ለረጅም ፡ ከፍታ ፡ በአንተ ፡ ልብ ፡ የታጩ
ከፈቃድህ ፡ ርቀው ፡ በአጭር ፡ ተቀጩ
እንዲያ ፡ ከመሆን ፡ አድነኝ ፡ ጌታ
ፈቃድህ ፡ ያግኘኝ ፡ ከጥፋት ፡ ፈንታ
የእኔ ፡ አይሁን ፡ ግዣኝ ፡ አባቴ
ያልያ ፡ ግን ፡ ውድቀት ፡ ነው ፡ ከንቱ ፡ ልፋቴ
አዎ ፡ ከንቱ ፡ ልፋቴ
ፈቃድህ ፡ እንደሆነች ፡ በሰማይ ፡ አምላኬ
እንዲሁ ፡ በምድርም ፡ ትሁን ፡ ጌታዬ (፪x)
አዝ፦ የወይኑ ፡ ቦታ ፡ አሄ ፡ እህህም ፡ የወይኑ ፡ ቦታ
አወይ ፡ የወይኑ ፡ ቦታ ፡ አሄ ፡ እህህም ፡ የወይኑ ፡ ቦታ
በአግባብ ፡ ተቆፍሮ ፡ አሄሄ ፡ ድንጋይም ፡ ተለቅሞ
ኦ ፡ ምርጥ ፡ የተባለ ፡ ዘር ፡ ከእርሱ ፡ ዘንዳ
ከእርሱ ፡ ዘንታ ፡ ተክሎ
ኧረ ፡ እኔስ ፡ አልገባኝም ፡ አሄሄ ፡ መራራ ፡ ማፍራቱ
ይህን ፡ ክፉ ፡ ፍሬ ፡ አሃሃም ፡ ለጌታው ፡ መስጠቱ
በፍሬያማው ፡ በዚያ ፡ ኮረብታ ፡ ላይ
በምድር ፡ ሆኜ ፡ ዜጋዬ ፡ የሰማይ
ዘመኔን ፡ ሙሉ ፡ አንተ ፡ እንድትገዛኝ
ፈቃዴን ፡ እሰጥሃለሁ ፡ መሻቴ ፡ ይህ ፡ ነው
ከእግሮቼ ፡ ስር ፡ ልሁን ፡ ጌታዬ
እርሱ ፡ ነው ፡ ክብር ፡ ያ ፡ ነው ፡ ምርጫዬ
አዎ ፡ ያ ፡ ነው ፡ ምርጫዬ
አዝ፦ የወይኑ ፡ ቦታ ፡ አሄ ፡ እህህም ፡ የወይኑ ፡ ቦታ
አወይ ፡ የወይኑ ፡ ቦታ ፡ አሄ ፡ እህህም ፡ የወይኑ ፡ ቦታ
በአግባብ ፡ ተቆፍሮ ፡ አሄሄ ፡ ድንጋይም ፡ ተለቅሞ
ኦ ፡ ምርጥ ፡ የተባለ ፡ ዘር ፡ ከእርሱ ፡ ዘንዳ
ከእርሱ ፡ ዘንታ ፡ ተክሎ
ኧረ ፡ እኔስ ፡ አልገባኝም ፡ አሄሄ ፡ መራራ ፡ ማፍራቱ
ይህን ፡ ክፉ ፡ ፍሬ ፡ አሃሃም ፡ ለጌታው ፡ መስጠቱ
የጌቴሴማኒ ፡ የእምባ ፡ ተክልህ
የቀራንዮ ፡ የደምህ ፡ ፍሬ ፡ ብቅለትህ
ጣዕሜ ፡ እንዳይሆን ፡ ደርሶ ፡ መራራ
ለመብል ፡ ሲታይ ፡ ሲያጐመራ
አምላኬ ፡ እግዚአብሔር ፡ ፈቅድህ ፡ ይግዛኝ
አውቃለሁ ፡ የእኔ ፡ ከቶ ፡ እንዳይጠቅመኝ
አዎ ፡ ከቶ ፡ አይጠቅመኝ
አዝ፦ የወይኑ ፡ ቦታ ፡ አሄ ፡ እህህም ፡ የወይኑ ፡ ቦታ
አወይ ፡ የወይኑ ፡ ቦታ ፡ አሄ ፡ እህህም ፡ የወይኑ ፡ ቦታ
በአግባብ ፡ ተቆፍሮ ፡ አሄሄ ፡ ድንጋይም ፡ ተለቅሞ
ኦ ፡ ምርጥ ፡ የተባለ ፡ ዘር ፡ ከእርሱ ፡ ዘንዳ
ከእርሱ ፡ ዘንታ ፡ ተክሎ
ኧረ ፡ እኔስ ፡ አልገባኝም ፡ አሄሄ ፡ መራራ ፡ ማፍራቱ
ይህን ፡ ክፉ ፡ ፍሬ ፡ አሃሃም ፡ ለጌታው ፡ መስጠቱ
|