የደስታ ፡ ዘይት (Yedesta Zeyt) - በረከት ፡ አለሙ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
በረከት ፡ አለሙ
(Bereket Alemu)

Bereket Alemu 1.jpg


(1)

ወዶ ፡ ዘማች
(Wedo Zemach)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፯ (2007)
ቁጥር (Track):

(7)

ርዝመት (Len.): 6:30
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የበረከት ፡ አለሙ ፡ አልበሞች
(Albums by Bereket Alemu)

መከራን ባየሁበት ዘመን
ክፉንም ባየሁበት ፈንታ
የ ደስታን ዘይት ከላዬ
አፈሰሰልኝ በላዬ
እየሱስ ጌታዬ(2) (2)
ለቅሶዬን በ ደስታ ቀየረልኝ
አሃሃ ቀየረልኝ
እምባዬን ካይኔ ላይ አበሰልኝ
አሃ አበሰልኝ
        አ ሃ ሃ ጠላቶች በኔ ላይ በተነሱ ጊዜ
        አ ሃ ሃ በ ፍርሃት ውስጥ ስባኝ
        ሆኜ በ ትካዜ (2)
        ሰላም ላንተ ብሎ
        ሃዘን ተከልክሎ (2)
        አሳዳጆቼ ወድቀው
        በ ዙሪያዬ አየሁ አሄ ሄ
        ባምላኬ ተመተው (2)

መከራን ባየሁበት ዘመን
ክፉንም ባየሁበት ፈንታ
የ ደስታን ዘይት ከላዬ
አፈሰሰልኝ በላዬ
እየሱስ ጌታዬ(2) (2)
ለቅሶዬን በ ደስታ ቀየረልኝ
አሃሃ ቀየረልኝ
እምባዬን ካይኔ ላይ አበሰልኝ
አሃ አበሰልኝ
አብሮነቱ ከኔ ጋር ሆነና
ኢየሱስ አብሮኝ ሆነና
ለዋውጦ ቀያይሮ አስዋበኛ
አቆመኝ እንደገና

        አዝማቼ !
        አዝማቸ ነው ከፊተ ሚወጣው
        በ ጦርነቴ ላይ ድልን የሚያመጣ (2)
        አስጨናቂዎቼን ባንድ ቃል በትኖ
        ተራመድ ብሎኛል ተራራውን ደልድሎ

ከ እንግዲማ ኖራለሁኝ
ያምላኬ ስም እየተጠራ
የኔ ኩራት ወጌ ማረጌ
ኢየሱሴ ደራሽ ለ ነፍሴ (4)