ተደስቻለሁ (Tedeschalehu) - በረከት ፡ አለሙ
From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
< Bereket Alemu | Wedo Zemach
Jump to: navigation, search
| በረከት ፡ አለሙ (Bereket Alemu) | |
|---|---|
|
፩ |
|
| ዓ.ም. (Year): | ፳ ፻ ፯ (2007) |
| ቁጥር (Track): |
፪ (2) |
| ርዝመት (Len.): | 10:22 |
| ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች (Other Songs in the Album) | |
| የበረከት ፡ አለሙ ፡ አልበሞች (Albums by Bereket Alemu) | |
ፍስም ፡ አልቀረልኝም (8)
ወደድኩህ ፡ ስትለኝ
ነፍስም ፡ አልቀረልኝም
ልጄ ፡ ነህ ፡ ስትለኝ
ነፍስም ፡ አልቀረልኝም
ጸድቀሃል ፡ ስትለኝ
ነፍስም ፡ አልቀረልኝም
ተርፈሃል ፡ ስትለኝ
ነፍስም ፡ አልቀረልኝም
ተደስቻለሁ ፡ እኔ ፡ ተደስቻለሁ
ባደራረግህ ፡ ኢየሱሴ ፡ ተደስቻለሁ
ተደስቻለሁ ፡ በቃ ፡ ተደስቻለሁ
ሰበብ ፡ ፈልጌ ፡ ፈላልጌ ፡ አመልክሃለሁ
ተገርሜአለሁ ፡ እኔ ፡ ተገርሜአለሁ
ባደራረግህ ፡ የኔ ፡ ወዳጅ ፡ ተገርሜአለሁ
ተደንቄአለሁ ፡ በቃ ፡ ተደንቄአለሁ
ሰበብ ፡ ፈልጌ ፡ ፈላልጌ ፡ አመልክሃለሁ
አዋፋት ፡ ሲያዜሙ ተራሮች ፡ ሲዘሉ ወንዙ ፡ ሲያመልክህ ባህር ፡ ሲታዘዙ አየሁ ፡ አየሁና ፡ ዙሪያዬን ፡ ቃኝቼ ሳጣ ፡ የማየውን ፡ አማትሬ ፡ አይቼ እኔም ፡ በ ፡ ተራዬ ደሞ ፡ የ ፡ ድርሻዬን ልወጣ ፡ አልኩና ያዝኩ ፡ በገናዬን የ ፡ ምስጋና ፡ ነዶ (2) ሊያቀርብልህ ፡ መጣ ልቤ ፡ አንተን ፡ ወዶ (2)
ተደስቻለሁ ፡ እኔ ፡ ተደስቻለሁ
ባደራረግህ ፡ ኢየሱሴ ፡ ተደስቻለሁ
ተደስቻለሁ ፡ በቃ ፡ ተደስቻለሁ
ሰበብ ፡ ፈልጌ ፡ ፈላልጌ ፡ አመልክሃለሁ
ተደስቻለሁ ፡ እኔስ ፡ ተደስቻለሁ
ባደራረግህ ፡ የኔ ፡ ኢየሱስ ፡ ተደስቻለሁ
ተገርሜአለሁ ፡ በቃ ፡ ተገርሜአለሁ
ሰበብ ፡ ፈልጌ ፡ ፈላልጌ ፡ አመልክሃለሁ
ቃል ፡ ሲወጣ ፡ ካፍህ ፡ ወደድኩህ (ወደድኩህ) ትኩረቴን ፡ ቀልቤን ፡ ገዛው ፡ ፈለኩህ በ ፡ አምልኮ ፡ በ ፡ ምስጋና ፡ ማደሪያህን አጥናለሁ ፡ በ ፡ እጣን ፡ ከርቤ ፡ ዙፋንህን
ተደስቻለሁ ፡ እኔ ፡ ተደስቻለሁ
ባደራረግህ ፡ ኢየሱሴ ፡ ተደስቻለሁ
ተደስቻለሁ ፡ በቃ ፡ ተደስቻለሁ
ሰበብ ፡ ፈልጌ ፡ ፈላልጌ ፡ አመልክሃለሁ
ተገርሜአለሁ ፡ እኔ ፡ ተገርሜአለሁ
ባደራረግህ ፡ የኔ ፡ ወዳጅ ፡ ተገርሜአለሁ
ተደንቄአለሁ ፡ በቃ ፡ ተደንቄአለሁ
ሰበብ ፡ ፈልጌ ፡ ፈላልጌ ፡ አመልክሃለሁ
ነፍሴ ፡ ደስ ፡ የሚላት ነፍሴ ፡ የምታርፈው በ ፡ ምስጋና ፡ በ ፡ አምልኮ ፡ ስትውል ፡ ነው (2) አላውቅም ፡ ሌላ ፡ ደስታ ፡ ከዚህ ፡ ውጪ ለኔ ፡ በቃ ፡ አልፈልግም ፡ ሌላ ፡ አማራጪ በ ፡ ህልውና ፡ መገኘቱ ፡ ውስጥ ፡ መኖሬ የ ፡ ኑሮዬ ፡ ልምምድ ፡ ነው ፡ መዘመሬ
አጥንቴም ፡ ስሜቴም ፡ ጅማቴም
ነፍሴ ፡ እና ፡ ቁርጭምጭሚቶቼም
ባንድላይ ፡ ለ ፡ ክብርህ ፡ ይዋሉ
ለተሰሩበት ፡ አላማ ፡ ሳይጎሉ
ተደስቻለሁ ፡ እኔ ፡ ተደስቻለሁ
ባደራረግህ ፡ ኢየሱሴ ፡ ተደስቻለሁ
ተደስቻለሁ ፡ በቃ ፡ ተደስቻለሁ
ሰበብ ፡ ፈልጌ ፡ ፈላልጌ ፡ አመልክሃለሁ
ተገርሜአለሁ ፡ እኔ ፡ ተገርሜአለሁ
ባደራረግህ ፡ የኔ ፡ ወዳጅ ፡ ተገርሜአለሁ
ተደንቄአለሁ ፡ በቃ ፡ ተደንቄአለሁ
ሰበብ ፡ ፈልጌ ፡ ፈላልጌ ፡ አመልክሃለሁ