ተደስቻለሁ (Tedeschalehu) - በረከት ፡ አለሙ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
በረከት ፡ አለሙ
(Bereket Alemu)

Bereket Alemu 1.jpg


(1)

ወዶ ፡ ዘማች
(Wedo Zemach)

ዓ.ም. (Year): 2007
ቁጥር (Track):

(3)

ርዝመት (Len.): 8:58
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የበረከት ፡ አለሙ ፡ አልበሞች
(Albums by Bereket Alemu)

ነፍስም ፡ አልቀረልኝም (8)
ወደድኩህ ፡ ስትለኝ
ነፍስም ፡ አልቀረልኝም
ልጄ ፡ ነህ ፡ ስትለኝ
ነፍስም ፡ አልቀረልኝም
ጸድቀሃል ፡ ስትለኝ
ነፍስም ፡ አልቀረልኝም
ተርፈሃል ፡ ስትለኝ
ነፍስም ፡ አልቀረልኝም

        ተደስቻለሁ ፡ እኔ ፡ ተደስቻለሁ
        ባደራረግህ ፡ ኢየሱሴ ፡ ተደስቻለሁ
        ተደስቻለሁ ፡ በቃ ፡ ተደስቻለሁ
        ሰበብ ፡ ፈልጌ ፡ ፈላልጌ ፡ አመልክሃለሁ
        ተገርሜአለሁ ፡ እኔ ፡ ተገርሜአለሁ
        ባደራረግህ ፡ የኔ ፡ ወዳጅ ፡ ተገርሜአለሁ
        ተደንቄአለሁ ፡ በቃ ፡ ተደንቄአለሁ
        ሰበብ ፡ ፈልጌ ፡ ፈላልጌ ፡ አመልክሃለሁ

አዋፋት ፡ ሲያዜሙ
ተራሮች ፡ ሲዘሉ
ወንዙ ፡ ሲያመልክህ
ባህር ፡ ሲታዘዙ
አየሁ ፡ አየሁና ፡ ዙሪያዬን ፡ ቃኝቼ
ሳጣ ፡ የማየውን ፡ አማትሬ ፡ አይቼ
እኔም ፡ በ ፡ ተራዬ
ደሞ ፡ የ ፡ ድርሻዬን
ልወጣ ፡ አልኩና
ያዝኩ ፡ በገናዬን
የ ፡ ምስጋና ፡ ነዶ (2)
ሊያቀርብልህ ፡ መጣ
ልቤ ፡ አንተን ፡ ወዶ (2)
         
           ተደስቻለሁ ፡ እኔ ፡ ተደስቻለሁ
           ባደራረግህ ፡ ኢየሱሴ ፡ ተደስቻለሁ
           ተደስቻለሁ ፡ በቃ ፡ ተደስቻለሁ
           ሰበብ ፡ ፈልጌ ፡ ፈላልጌ ፡ አመልክሃለሁ
           ተደስቻለሁ ፡ እኔስ ፡ ተደስቻለሁ
           ባደራረግህ ፡ የኔ ፡ ኢየሱስ ፡ ተደስቻለሁ
           ተገርሜአለሁ ፡ በቃ ፡ ተገርሜአለሁ
           ሰበብ ፡ ፈልጌ ፡ ፈላልጌ ፡ አመልክሃለሁ

ቃል ፡ ሲወጣ ፡ ካፍህ ፡ ወደድኩህ (ወደድኩህ)
ትኩረቴን ፡ ቀልቤን ፡ ገዛው ፡ ፈለኩህ
በ ፡ አምልኮ ፡ በ ፡ ምስጋና ፡ ማደሪያህን
አጥናለሁ ፡ በ ፡ እጣን ፡ ከርቤ ፡ ዙፋንህን

            ተደስቻለሁ ፡ እኔ ፡ ተደስቻለሁ
            ባደራረግህ ፡ ኢየሱሴ ፡ ተደስቻለሁ
            ተደስቻለሁ ፡ በቃ ፡ ተደስቻለሁ
            ሰበብ ፡ ፈልጌ ፡ ፈላልጌ ፡ አመልክሃለሁ
            ተገርሜአለሁ ፡ እኔ ፡ ተገርሜአለሁ
            ባደራረግህ ፡ የኔ ፡ ወዳጅ ፡ ተገርሜአለሁ
            ተደንቄአለሁ ፡ በቃ ፡ ተደንቄአለሁ
            ሰበብ ፡ ፈልጌ ፡ ፈላልጌ ፡ አመልክሃለሁ

ነፍሴ ፡ ደስ ፡ የሚላት
ነፍሴ ፡ የምታርፈው
በ ፡ ምስጋና ፡ በ ፡ አምልኮ ፡ ስትውል ፡ ነው
(2)
አላውቅም ፡ ሌላ ፡ ደስታ ፡ ከዚህ ፡ ውጪ
ለኔ ፡ በቃ ፡ አልፈልግም ፡ ሌላ ፡ አማራጪ
በ ፡ ህልውና ፡ መገኘቱ ፡ ውስጥ ፡ መኖሬ
የ ፡ ኑሮዬ ፡ ልምምድ ፡ ነው ፡ መዘመሬ


አጥንቴም ፡ ስሜቴም ፡ ጅማቴም
ነፍሴ ፡ እና ፡ ቁርጭምጭሚቶቼም
ባንድላይ ፡ ለ ፡ ክብርህ ፡ ይዋሉ
ለተሰሩበት ፡ አላማ ፡ ሳይጎሉ
     
            ተደስቻለሁ ፡ እኔ ፡ ተደስቻለሁ
            ባደራረግህ ፡ ኢየሱሴ ፡ ተደስቻለሁ
            ተደስቻለሁ ፡ በቃ ፡ ተደስቻለሁ
            ሰበብ ፡ ፈልጌ ፡ ፈላልጌ ፡ አመልክሃለሁ
            ተገርሜአለሁ ፡ እኔ ፡ ተገርሜአለሁ
            ባደራረግህ ፡ የኔ ፡ ወዳጅ ፡ ተገርሜአለሁ
            ተደንቄአለሁ ፡ በቃ ፡ ተደንቄአለሁ
            ሰበብ ፡ ፈልጌ ፡ ፈላልጌ ፡ አመልክሃለሁ