ሽልማቴ (Shelemate) - በረከት ፡ አለሙ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
በረከት ፡ አለሙ
(Bereket Alemu)

Bereket Alemu 1.jpg


(1)

ወዶ ፡ ዘማች
(Wedo Zemach)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፯ (2007)
ቁጥር (Track):

(1)

ርዝመት (Len.): 4:47
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የበረከት ፡ አለሙ ፡ አልበሞች
(Albums by Bereket Alemu)

ጌጤ ፡ ወርቄ ፡ ውበቴ ፡ ደም ፡ ግባቴ
ኢየሱሴ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ሽልማቴ (2)
ሽልማቴ ፡ ሽልማቴ
ኢየሱሴ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ሽልማቴ (2)
        
              ከ ፡ ነገድ ፡ ቋንቋ ፡ በ ፡ ልጁ ፡ የዋጀኝ
              ወደከበረ ፡ መንግስቱ ፡ ያፈለሰኝ
              ከላይ ፡ ሲመጣ ፡ የተቀበልኩት ፡ ስጦታዬ
              ወራሽ ፡ አረገኝ ፡ የ ፡ እርስቱ ፡ ተካፋይ (5)

ሽልማቴ ፡ ሽልማቴ
ኢየሱሴ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ሽልማቴ (2)
      
             እኔን ፡ ለማድረግ ፡ ባለጠጋ ፡ ሆነህ ፡ ባዶ
             ውበት ፡ ሊሰጠኝ ፡ በኔ ፡ ምትክ ፡ ተሰቃይቶ
             በሰማያዊ ፡ በረከቱ ፡ ባረከኝ
             በ ፡ ጸጋው ፡ ሙላት ፡ በ ፡ መንፈሱ ፡ ከበበኝ (5)

ሽልማቴ ፡ ሽልማቴ
ኢየሱሴ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ሽልማቴ (2)
      
             የታረደው ፡ ኢየሱስ ፡ ፋሲካዬ
             የሞትን ፡ ጣር ፡ ገፈፈልኝ ፡ ከላዬ
             ዳግም ፡ ህይወት ፡ አገኘሁ ፡ ታደስኩኝ
             የ ፡ እግዚአብሄር ፡ ልጅ ፡ በመሆን ፡ ጸደኩኝ
                       አ ፡ ሃ ፡ ሃ ፡ ጸደኩኝ (2)
                       አ ፡ ሃ ፡ ሃ ፡ ከፍ ፡ አልኩኝ (2)
                       አ ፡ ሃ ፡ ሃ ፡ ከበርኩኝ (2)
                       አ ፡ ሃ ፡ ሃ (2)
ማንም ፡ የተጠማ ፡ ይምጣና
ከ ፡ ህይወት ፡ ውሃ ፡ ይጠጣና
በ ፡ ሰላም ፡ ይኑር ፡ በ ፡ እርጋታ
ብሎ ፡ ተናግሮአል ፡ ይሄ ፡ ጌታ
እኔም ፡ ሰማሁት ፡ ወዳጄን
የ ፡ ህይወት ፡ መንገድ ፡ መሪዬን
ውጬዋለሁኝ ፡ መድሃኒቴን
አትርፌአታለሁ ፡ ይህች ፡ ነፍሴን

ሽልማቴ ፡ ሽልማቴ
ኢየሱሴ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ሽልማቴ (2)