ለወንጌል (Lewengel) - በረከት ፡ አለሙ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
በረከት ፡ አለሙ
(Bereket Alemu)

Bereket Alemu 1.jpg


(1)

ወዶ ፡ ዘማች
(Wedo Zemach)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፯ (2007)
ቁጥር (Track):

(5)

ርዝመት (Len.): 5:17
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የበረከት ፡ አለሙ ፡ አልበሞች
(Albums by Bereket Alemu)

እ ፡ የ ፡ እግዚአብሄር ፡ ልጅ
ያባቴ ፡ ልጅ
የ ፡ ወንጌል ፡ ፍሬ
በሞቱ ፡ ታድጎ ፡ ዘር ፡ ያረገህ ፡ ሆይ
የ ፡ እግዚአብሄር ፡ ልጅ
ያባቴ ፡ ልጅ
እ ፡ እስኪ ፡ ለ ፡ ጌታ
ለ ፡ ወዳጄማ ፡ ለ ፡ ኢየሱሴ
አለምን ፡ ቢኮንን ፡ ቢያከብረው ፡ ህይወቴ
ለ ፡ ወዳጄማ ፡ ለ ፡ ኢየሱሴ

ብኖርለት ፡ ብንሆንለት
ለ ፡ ወንጌሉ ፡ ደግሞስ ፡ ቢሞትለት

ከኖሩስ ፡ ለ ፡ ወንጌል
ከ ፡ ሞቱስ ፡ ለ ፡ ወንጌል
ህይወት ፡ ከሰጡ ፡ አይቀር
አክሊል ፡ ላለው ፡ ነገር
እንደ ፡ ቀደሙቱ
እንደ ፡ ሃዋርያቱ
ወንጌሉን ፡ አምነውት ፡ ለ ፡ እርሱ ፡ እንደሞቱ

          እኔም ፡ ባለኝ ፡ ባጭር ፡ ዘመኔ
          ኖሬ ፡ ልለፍ ፡ ለዚህ ፡ መድኔ
          በጊዜውም ፡ ያለጊዜውም
          የ ፡ ወንጌሉ ፡ ቃል ፡ ይሰማ ፡ ላለም (፪)

ማነው ፡ ደፋር
ማነው ፡ ጀግና
የቆረጠ
ላለም ፡ የሞተ
እንደ ፡ ጳውሎስ
እንደ ፡ ጴጥሮስ
ሞአች ፡ ተጋዳይ
ገብቶት ፡ ህይወት

          እ ፡ ምድራዊ ፡ ኑሮ ፡ ያላሮጣቸው ፡ ያላጉዋጉዋቸው
          ጌታን ፡ ??? ፡ ሆኖ ፡ ራባቸው

በ ፡ ምድር ፡ እያሉ
ለ ፡ ሰማይ ፡ ሚኖሩ
ለ ፡ ድካም ፡ ስንፍና
ጥቅስ ፡ ያልደረደሩ
ለ ፡ አለም ፡ ለ ፡ ዝና
ጥቅም ፡ ያላደሩ
ለ ፡ ወንጌል ፡ አደራ
ታምነው ፡ የከበሩ

ይሄን ፡ ምድር ፡ የተውንበት
ይሄን ፡ ምድር ፡ የናቅንበት
አለን ፡ እርስት ፡ አለን ፡ ክብር
አልን ፡ አባት ፡ አለን ፡ ጌታ
ለዚች ፡ አለም ፡ የሞትንበት
ሰማይ ፡ ሰማይ ፡ የምንልበት
አለን ፡ እርስት ፡ አለን ፡ ክብር
አልን ፡ አባት ፡ አለን ፡ ጌታ

             መከራውን ፡ አልፈሩም
             ችግሩን ፡ አልፈሩም
             እስራት ፡ አልፈሩም
             መሞትን ፡ አልፈሩም

               በጸጋው ፡ ብርታት(አሃሃ ሃ ሃ ሃ ሃ)
               ሃይል ፡ እየታገዙ (አሃሃ ሃ ሃ ሃ)
               በክብር ፡ በመንፈሱ (አሃሃ ሃ ሃ ሃ)
               ሄዱ ፡ ገሰገሱ (አሃሃ ሃ ሃ ሃ)(፪)

ማነው ፡ ደፋር
ማነው ፡ ጀግና
የቆረጠ
ላለም ፡ የሞተ
እንደ ፡ ጳውሎስ
እንደ ፡ ጴጥሮስ
ሞአች ፡ ተጋዳይ
ገብቶት ፡ ህይወት