አልረሳውም (Alresawem) - በረከት ፡ አለሙ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
በረከት ፡ አለሙ
(Bereket Alemu)


(1)

ወዶ ፡ ዘማች
(Wedo Zemach)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፯ (2015)
ቁጥር (Track):

(4)

ርዝመት (Len.): 5:54
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የበረከት ፡ አለሙ ፡ አልበሞች
(Albums by Bereket Alemu)

           ያደረክልኝን ፡ ውለታ
           በምንም ፡ በምንም ፡ አልረሳም
           ከየት ፡ እንዳነሳኸኝ
           በምንም ፡ በምንም ፡ አልረሳም (፪x)

ከትላንቱ ፡ ለሊት ፡ ካስፈሪው
ከዚያ ፡ ከጨለማ
ነጥቀህ ፡ ስታወጣኝ ፡ ኢየሱስ
ማነው ፡ በዓይኑ ፡ ያላየ
ማነው ፡ ጆሮው ፡ ያልሰማ
ቁሻሻዬን ፡ ሸክሜን ፡ አራግፈህ
ሰው ፡ ስታደርገኝ

           ያደረክልኝን ፡ ውለታ
           በምንም ፡ በምንም ፡ አልረሳም (፭x)

መነሻ ፡ እንደሌለው ፡ መድረሻዬ ፡ ላይ ፡ ቆሜ
የምሥጋና ፡ ቃሌን ፡ ለማጠፍ ፡ የረዳኝን ፡ ወዲያ ፡ ብዬ
ከእናቴ ፡ ማህጸን ፡ ስወጣ ፡ በስኬት ፡ ካባ ፡ ተሽሜ
ይህ ፡ ይመስል ፡ አልነካኝ ፡ ነፋሱ ፡ የማለፊያው ፡ የችግሬ
እኔም ፡ እንዳልሆነ ፡ አላወራም ፡ ቆሜ

ማን ፡ ረድቶኝ ፡ ማን ፡ አግዞኝ ፡ አልልም (፫x)
ጉልበቴ ፡ አመጣልኝ ፡ አልልም (፫x)
ጥበቤ ፡ በዝቶ ፡ እውቀቴ ፡ አልልም (፫x)
ያከማቸሁት ፡ ይህ ፡ ሃብቴ ፡ አልልም (፫x)

       አላስብም ፡ እንደበረታሁ
       አላስብም ፡ ከእግዚአብሄር/ከፀጋው ፡ ውጪ
       አላስብም ፡ በጉብዝናዬ
       አላስብም ፡ አለፍኩት ፡ ብዬ (፪x)
        
ከልጅነቴ ፡ እስከ ፡ እውቀቴ
ያሳደከኝ ፡ ያስተማርከኝ (፪x)
በፍቅር ፡ እጅህ ፡ አጉርሰኸኛል
መምህሬ ፡ ነህ ፡ መች ፡ ይረሳኛል (፪x)
           
ውጪውን ፡ አላየውም ፡ ላፍታ
አልደሰት ፡ በግብዝ ፡ ትዝታ
ገብቶኛል ፡ በቤቴ ፡ ያረከው
አብዝተህ ፡ ለእኔ ፡ ያትረፈረፍከው (፪x)

በእጄ ፡ ያለው ፡ ወርቅ ፡ አይሁንብኝ (፪x)
አላቀለውም ፡ አይወድቅብኝም (፪x)
በአንተ ፡ ጉያ ፡ ነው ፡ ዘላለሜ (፪x)
ስምህ ፡ ሆንዋል ፡ የኑሮ ፡ አለሜ (፪x)
ና ና ና ና ና ና (4)

       ውለታህ ፡(አልረሳም)
       ጥበቃህን ፡(አልረሳም)
       ምህረትን ፡ (አልረሳም)
       እኔ ፡ አልረሳም ፡ (አልረሳም)
       ምህረትን ፡ (አልረሳም)
       ፍቅርህን ፡ (አልረሳም)
       ያረከውን ፡ (አልረሳም)
       ከቶ ፡ አልረሳም ፡ (አልረሳም)
       አልረሳም

       ውለታህን ፡ (አልረሳም)
       ጥበቃህን ፡ (አልረሳም)
       ፍቅርህን ፡ (አልረሳም)
       እኔ ፡ አልረሳም ፡ (አልረሳም)
       አሃ ፡ እኔ ፡ አልረሳም ፡ (አልረሳም)
       ዎዎው ፡ (አልረሳም)
       ኢየሱሴ ፡ (አልረሳም)