Yohannes (Belay)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ



ነፍሴም ፡ እንደ ፡ ውኃ ፡ አንተን ፡ ተጠማች በቀንም ፡ በማታም ፡ እየናፈቀች (፪x) ያሰብኩት ፡ ተሳክቶ ፡ እርካታ ፡ ሳይኖረኝ ኢየሱስ ፡ ግን ፡ ሲመጣ ፡ ህይወት ፡ ፈለቀልኝ (፪x)

እኔማ ፡ አላይ ፡ ወደሌላ የልቤ ፡ ሚገባው ፡ ሌላ ፡ የለምና ኑሮዬም ፡ ቢሞላ ፡ ሚመች እርካታዬ ፡ ኢየሱስ ፡ ስለሆነ ፡ እንጂ

ደመና ፡ አልባ ፡ ሰማይ ፡ ተንጣሎ ፡ ከፊቴ ወጀብ ፡ ሲያፏጭባት ፡ ተፋልሳ ፡ ሕይወቴ በማይቋጭ ፡ ዙሪት ፡ ተስፋ ፡ አጥቼ ፡ ሳለሁ የዘላለም ፡ ተስፋ ፡ ኢየሱስን ፡ አገኘው (፪x)

እኔማ ፡ አላይ ፡ ወደሌላ ፡ እርካታ ፡ ሚሞላ ፡ ሌላ ፡ የለምና ኑሮዬም ፡ ቢሞላ ፡ ሚመች እርካታዬ ፡ ኢየሱስ ፡ ስለሆነ ፡ እንጂ

በልቶም ፡ ይርበዋል ፡ አግኘቶ ፡ ይጐለዋል ዛሬ ፡ አገኘሁኝ ፡ ሲል ፡ ኪሳራ ፡ ይቀድመዋል ከምንጩ ፡ የሸሸ ፡ ነፍስ ፡ ከአንተ ፡ ርቆ ፡ የሄደ የወጣ ፡ ሲመስለው ፡ ወደታች ፡ ወረደ (፪x)

እኔማ ፡ አላይ ፡ ወደሌላ እርካታ ፡ ሚሞላ ፡ ሌላ ፡ የለምና ኑሮዬም ፡ ቢሞላ ፡ ሚመች እርካታዬ ፡ ኢየሱስ ፡ ስለሆነ ፡ እንጂ

እርካታዬ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው እርካታዬ (፰x)