From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
አዝ:- ዋስ ፡ ጠበቃዬ (፪x) ፡ ካህኔ
ኢየሱስ ፡ የነፍስ ፡ አባቴ (፬x)
የእርግብ ፡ የፍየል ፡ ደም ፡ ይፍሰስ
መሰዊያ ፡ ላድርጋቸው ፡ እንድዱት
የህዝቡ ፡ ኀጢአት ፡ እንዲሰረይለት
ሚቃጠል ፡ መስዋዕት ፡ ይቅረብለት
ይህ ፡ ስርአት ፡ ቀረ (፬x)
መስዋዕቴ ፡ ኢየሱስ ፡ ሆነ
መስዋዕቴ ፡ የከበረ (፪x)
አዝ:- ዋስ ፡ ጠበቃዬ (፪x) ፡ ካህኔ
ኢየሱስ ፡ የነፍስ ፡ አባቴ (፬x)
ኀጢአትን ፡ ማስወገድ ፡ የማይችሉ
መስዋዕት ፡ ሁልጊዜ ፡ ሲያቅርቡ
እርሱ ፡ ግን ፡ ለአንዴ ፡ ፈጽሞ
ቀደሰኝ ፡ እራሱን ፡ አቅርቦ
የአዲስ ፡ ኪዳን ፡ ልጅ ፡ ነኝ (፬x)
የተሻለ ፡ ካህን ፡ አለኝ
የተሻለ ፡ ኪዳን ፡ አለኝ (፪x)
አዝ:- ዋስ ፡ ጠበቃዬ (፪x) ፡ ካህኔ
ኢየሱስ ፡ የነፍስ ፡ አባቴ (፬x)
ቃልኪዳን ፡ ከእኔ ፡ ጋር ፡ አደረገ
ህጉንም ፡ በልቤ ፡ አስቀመጠ
በአዲስና ፡ በሕያው ፡ መንገድ
አስገባኝ ፡ በስጋው ፡ በደም
የአዲስ ፡ ኪዳን ፡ ልጅ ፡ ነኝ (፬x)
የተሻለ ፡ ካህን ፡ አለኝ
የተሻለ ፡ ኪዳን ፡ አለኝ (፪x)
አዝ:- ዋስ ፡ ጠበቃዬ (፪x) ፡ ካህኔ
ኢየሱስ ፡ የነፍስ ፡ አባቴ (፬x)
እግዚአብሔር ፡ የራሱን ፡ ፍቅር ፡ የገለጠበት
ስጦታው ፡ እንዴት ፡ ካለ ፡ ሞት ፡ እኔን ፡ ያዳነበት
ተአምር ፡ የምለው ፡ በሕይወቴ
ኢየሱሴ ፡ የነፍስ ፡ አባቴ
ኦ ፡ ኢየሱሴ ፡ የነፍስ ፡ አባቴ (፪x)
የውስጤን ፡ ሁሉ ፡ ማሳየው ፡ ሚስጥረኛዬ
በአብ ፡ ቀኝ ፡ የሚቆምልኝ ፡ ጠበቃዬ
ሚረዳኝ ፡ ደግሞም ፡ ሚረዳኝ ፡ ሊቀ ፡ ካህኔ
ኢየሱሴ ፡ የነፍስ ፡ አባቴ
ኦ ፡ ኢየሱሴ ፡ የነፍስ ፡ አባቴ (፮x)
|