ተይ ፡ ነፍሴ (Tey Nefsie) - አዜብ ፡ መለሰ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አዜብ ፡ መለሰ
(Azeb Melesse)

Azeb Melesse 1.jpeg

(1)

የነፍስ ፡ አባቴ
(Yenefs Abatie)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፬ (2011)
ቁጥር (Track):

(6)

ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአዜብ ፡ መለሰ ፡ አልበሞች
(Albums by Azeb Melesse)

አዝ:- ተይ ፡ ነፍሴ ፡ ከመንገድ ፡ አትቅሪ
ተይ ፡ ነፍሴ ፡ ምድረ ፡ በዳ ፡ አትቅሪ
(፪x)
እርስት ፡ አለ ፡ ተነሽ ፡ እሩጪ ፣ መኖሪያ ፡ አለ ፡ ተነሽ ፡ እሩጪ
ክብር ፡ አለ ፡ ተነሽ ፡ እሩጪ ፣ አክሊል ፡ አለ ፡ ተነሽ ፡ እሩጪ

ነፍሴ ፡ ሆይ ፡ እባክሽን ፡ ስሚ ፣ ልምከርሽ ፡ በደምብ ፡ አስተውዪ
እያቸው ፡ በምድር ፡ የሚሮጡ ፣ ለሚጠፋው ፡ አክሊል ፡ ሲተጉ
እርግጥ ፡ ነው ፡ ክርስትና ፡ ያማል ፣ ከኖሩ ፡ ዋጋ ፡ ያስከፍላል
ከታገልሽ ፡ ሁሉም ፡ ነገር ፡ ያልፋል ፣ ጠብቂ ፡ ኢየሱስ ፡ ይመጣል

አዝ:- ተይ ፡ ነፍሴ ፡ ከመንገድ ፡ አትቅሪ
ተይ ፡ ነፍሴ ፡ ምድረ ፡ በዳ ፡ አትቅሪ
(፪x)
እርስት ፡ አለ ፡ ተነሽ ፡ እሩጪ ፣ መኖሪያ ፡ አለ ፡ ተነሽ ፡ እሩጪ
ክብር ፡ አለ ፡ ተነሽ ፡ እሩጪ ፣ አክሊል ፡ አለ ፡ ተነሽ ፡ እሩጪ

እረኛ ፡ እንደሌለሽ ፡ አትሁኚ ፣ እንደማንም ፡ መንገድ ፡ ላይ ፡ አትቅሪ
ስጋሽን ፡ ጉሽም ፡ አድርገሽ ፡ ይዘሽ ፣ ወደ ፡ ርስትሽ ፡ ግቢ ፡ ጨክነሽ
ችግሩን ፡ መከራውን ፡ መቅመስ ፣ ግድ ፡ ነው ፡ ብድረ ፡ በዳን ፡ ማለፍ
በሜዳው ፡ በትዕግስት ፡ እሩጪ ፣ አቃተኝ ፡ ብለሽ ፡ አታቋርጬ

አዝ:- ተይ ፡ ነፍሴ ፡ ከመንገድ ፡ አትቅሪ
ተይ ፡ ነፍሴ ፡ ምድረ ፡ በዳ ፡ አትቅሪ
(፪x)
እርስት ፡ አለ ፡ ተነሽ ፡ እሩጪ ፣ መኖሪያ ፡ አለ ፡ ተነሽ ፡ እሩጪ
ክብር ፡ አለ ፡ ተነሽ ፡ እሩጪ ፣ አክሊል ፡ አለ ፡ ተነሽ ፡ እሩጪ

ዮሴፍን ፡ ወንድሞቹ ፡ የጠሉት ፣ ለአውሬ ፡ ጉድጓድ ፡ ውስጥ ፡ የጣሉት
ያ ፡ ሁሉ ፡ ግፍ ፡ የደረሰበት ፣ የእግዚአብሔር ፡ ሃሳብ ፡ ስላለበት
እንዲህ ፡ ያለው ፡ ምስክር ፡ እያለሽ ፣ ተይ ፡ ነፍሴ ፡ ለምን ፡ ትደክሚያለሽ
ፈተና ፡ ለጊዜው ፡ ያሳዝናል ፣ ኋላ ፡ ላይ ፡ መልካም ፡ ፍሬ ፡ ያፈራል

አዝ:- ተይ ፡ ነፍሴ ፡ ከመንገድ ፡ አትቅሪ
ተይ ፡ ነፍሴ ፡ ምድረ ፡ በዳ ፡ አትቅሪ
(፪x)
እርስት ፡ አለ ፡ ተነሽ ፡ እሩጪ ፣ መኖሪያ ፡ አለ ፡ ተነሽ ፡ እሩጪ
ክብር ፡ አለ ፡ ተነሽ ፡ እሩጪ ፣ አክሊል ፡ አለ ፡ ተነሽ ፡ እሩጪ

እግዚአብሔር ፡ የሰጠሽን ፡ ተስፋ ፣ ሚያስጥሉ ፡ ብዙ ፡ ናቸውና
አንቺ ፡ ግን ፡ ታላቅ ፡ ዋጋ ፡ እንዳለሽ ፣ አትዘንጊ ፡ ምድራዊውን ፡ አይተሽ
የእምነትሽን ፡ ጀማሪ ፡ ፈጻሜ ፣ ምሳሌሽን ፡ ኢየሱስን ፡ እዬ
ጨርሰሽ ፡ የጀመርሺውን ፣ ተቀበይ ፡ ሽልማትሽን