ቅድስና (Qedesena) - አዜብ ፡ መለሰ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አዜብ ፡ መለሰ
(Azeb Melesse)

Azeb Melesse 1.jpeg


(1)

የነፍስ ፡ አባቴ
(Yenefs Abatie)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፬ (2011)
ቁጥር (Track):

፲ ፪ (12)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአዜብ ፡ መለሰ ፡ አልበሞች
(Albums by Azeb Melesse)

 
ኧረ ፡ እንዴት (፫x) ፡ ላምልክህ
ኧረ ፡ እንዴት ፡ ልሁንልህ
ኧረ ፡ እንዴት ፡ ላስደስትህ ፡ ጌታዬ
ኧረ ፡ እንዴት ፡ ልሁንልህ

ብዘምር ፡ ባከብርህ ፡ ይሄ ፡ ያረካሃል
ወይስ ፡ ብሰብክልህ ፡ የቱ ፡ ይሻልሃል
ልወቀው ፡ አምላኬ ፡ ምን ፡ ያስደስትሃል

"ልጄ ፡ ሆይ ፡ አዳምጪ"

መዘመር ፡ መስበኩ ፡ ማሸብሸብ ፡ መዝለሉ
ምን ፡ ያደርግልኛል ፡ መሰዋት ፡ ማብዛቱ
የኔ ፡ ልብ ፡ በደስታ ፡ ሃሴት ፡ የሚያደርገው
በሁለንተናሽን ፡ ስትቀደሺ ፡ ነው
ምታደርጊው ፡ ሁሉ ፡ በፊቴ ፡ ሞገስ ፡ የሚያገኘው
 
ዐይኖቼ ፡ ሁልጊዜ ፡ ሚመለከቱት
መንፈሱ ፡ ወደተሰበረው ፡ ትሁት
በቃሌ ፡ ወደሚንቀጠቀጥ ፡ ሰዉ
በሚፈራኝ ፡ እደሰታለሁ

ታዲያ ፡ ይሄ ፡ ካስደሰተህ
ታዲያ ፡ ይሄ ፡ ካረካህ
ልቀደስልህ ፡ ጌታዬ ፡ ልቀደስልህ
ልቀደስልህ ፡ አምላኬ ፡ ልቀደስልህ
ያለ ፡ ቅድስና ፡ እግዚአብሔርን ፡ ማየት ፡ አይቻልምና
ሁሌ ፡ ልቀደስ
ያለ ፡ ቅድስና ፡ እግዚአብሔርን ፡ ደስ ፡ ማሰኘት ፡ አይቻልምና
ሁሌ ፡ ልቀደስ

በሕይወቴ ፡ አክብሬ ፡ አንተን ፡ አገልግዬ
የዓለምን ፡ ምኞት ፡ ኀጢአት ፡ እምቢ ፡ ብዬ
በእኔ ፡ ደስ ፡ እንዲልህ ፡ ነውና ፡ አላማዬ
እኖርልሃለሁ ፡ በቅድስናዬ (፪x)