ቀደም ፡ ቢል ፡ ምን ፡ አለ (Qedem Bil Men Ale) - አዜብ ፡ መለሰ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
አዜብ ፡ መለሰ
(Azeb Melesse)

Azeb Melesse 1.jpeg


(1)

የነፍስ ፡ አባቴ
(Yenefs Abatie)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፬ (2011)
ቁጥር (Track):

(10)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአዜብ ፡ መለሰ ፡ አልበሞች
(Albums by Azeb Melesse)

 
ወይ ፡ አለማወቄ ፡ መጠንከሩ ፡ ልቤ
የተረኩልኝን ፡ ይዤ ፡ አለቅ ፡ ማለቴ
እምነት ፡ ከመስማት ፡ ነው ፡ መስማትም ፡ በቃሉ
እንደተንተራስኩት ፡ ዘመን ፡ ተቆጠሩ
ፀሐይ ፡ ስትጠልቅ ፡ ጥላው ፡ ሲሸሽም ፡ ማታ
ጉብዝናው ፡ ካለፈ ፡ ቢደርስልኝ ፡ ጌታ

አዝ:- ባለኝ ፡ ይሄ ፡ መልካም ፡ ነገር
ቀደም ፡ ቢል ፡ ምን ፡ አለ (፬x)

ጥርስ ፡ ከነቀልኩበት ፡ ከአደኩበት ፡ ቤቴ
አልለይም ፡ እያልኩ ፡ ከእናት ፡ ከአባቴ
ይማህተም ፡ ለውጥ ፡ የማደርግ ፡ መስሎኝ
ለካ ፡ የመንግሥት ፡ ነው ፡ ይሄ ፡ መቼ ፡ ገብቶኝ
ወደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ግዛት ፡ ፈቅጄ ፡ ብገባ
ሰብሮ ፡ ቢያላቅቀኝ ፡ ከዚያ ፡ ከጨለማስ

አዝ:- ባለኝ ፡ ይሄ ፡ መልካም ፡ ነገር
ቀደም ፡ ቢል ፡ ምን ፡ አለ (፬x)

መናኛውም ፡ ከፊት ፡ መልካሙም ፡ ከኋላ
እንዲሁ ፡ በደመነፍስ ፡ ነበር ፡ የኔ ፡ ስራ
ከዛ ፡ ተረት ፡ ተረት ፡ ሕይወት ፡ ውስጥ ፡ አውጥቶ
መንገድ ፡ ቢያስጀምረኝ ፡ ትርጉም ፡ ላለው ፡ ኑሮ
ቃሉ ፡ ቢጣፍጠኝ ፡ እንደ ፡ ማር ፡ ወለላ
ልቤን ፡ ዘልቆ ፡ ፍቅሩ ፡ ውስጥ ፡ ውስጤ ፡ ቢገባስ

አዝ:- ባለኝ ፡ ይሄ ፡ መልካም ፡ ነገር
ቀደም ፡ ቢል ፡ ምን ፡ አለ (፬x)

በከንቱ ፡ ያለፉት ፡ እነዚያ ፡ ቀኖቼ
ሳስበው ፡ ይቆጨኛል ፡ የዛሬን ፡ አይቼ
ዓለምን ፡ ሳይቀጫት ፡ ወይ ፡ እርሷ ፡ ሳትቀጨው
ብላቴና ፡ ሆኖ ፡ አንተን ፡ ላገኘ ፡ ሰው
ምንም ፡ እንደማያቅ ፡ ሞኝ ፡ ነው ፡ ቢሉትም
እንደእርሱስ ፡ ብልጥ ፡ የለም ፡ አላስተዋሉትም

አዝ:- እውነት ፡ ነው ፡ በጊዜ ፡ የበራለት
እርሱ ፡ እድለኛ ፡ ነው (፬x)