ንቃ (Neqa) - አዜብ ፡ መለሰ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አዜብ ፡ መለሰ
(Azeb Melesse)

Azeb Melesse 1.jpeg


(1)

የነፍስ ፡ አባቴ
(Yenefs Abatie)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፬ (2011)
ቁጥር (Track):

(4)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአዜብ ፡ መለሰ ፡ አልበሞች
(Albums by Azeb Melesse)

 
ያልተማረውን ፡ ተመራማሪ
የዚ ፡ ቤት ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ ባለዲግሪ
ያሞካሹታል ፡ በዘፈናቸው
ያቺኑ ፡ ሳንቲም ፡ እንዲሰጣቸው
(ኦ) ሆያ ፡ ሆያ ፡ ሆዬ ፡ ሆ (፪x)

ይህ ፡ ሆያ ፡ ሆዬ ፡ መልኩን ፡ ቀይሮ
ትንቢት ፡ በሚለው ፡ ስም ፡ ተሸፍኖ
እውነት ፡ በሚመስል ፡ ፍፁም ፡ ድራማ
ተቀነባብሮ ፡ እኛም ፡ ቤት ፡ ገባ

አዝ:- ንቃ ፡ ክርስቲያን ፡ ንቃ
በሐሰት ፡ ነቢያት ፡ አትዘናጋ (፪x)

ሰው ፡ እንደልቡ ፡ ዝሙትን ፡ ሰርቶ
በእርኩሰትና ፡ በአመጽ ፡ ተሞልቶ
ብለው ፡ ይሉታን ፡ አንተ ፡ ጐበዝ
እግዚአብሔር ፡ መጣ ፡ ሊባርክህ
(ኦ) ሆያ ፡ ሆያ ፡ ሆዬ ፡ ሆ (፪x)

ሰርቆ ፡ አጭበርብሮ ፡ የሚያመጣውን
መልካም ፡ ነው ፡ ብሎ ፡ ቢሰጥ ፡ ገንዘቡን
የበለጠውን ፡ ደግሞ ፡ እንዲያመጣ
አበዛዋለሁ ፡ ይልሃል ፡ ጌታ
(ኦ) ሆያ ፡ ሆያ ፡ ሆዬ ፡ ሆ (፪x)

ትክክለኛ ፡ ነቢዮች ፡ አሉ
የጌታን ፡ ብቻ ፡ የሚናገሩ
እነርሱንማ ፡ መች ፡ ሊሰሟቸው
ደፍሮ ፡ ይሏቸዋል ፡ ሟርተኛች ፡ ናቸው

አዝ:- ንቃ ፡ ክርስቲያን ፡ ንቃ
በሐሰት ፡ ነቢያት ፡ አትዘናጋ (፪x)

መንፈስ ፡ ቅዱስን ፡ ቃሉ ፡ እንደሚለው
ሌባውን ፡ ሌባ ፡ ጨዋ ፡ አይለው
አንተ ፡ ያልሆንከውን ፡ ነህ ፡ የሚልህ
ሊጠቅም ፡ አይደለም ፡ ነው ፡ ሊገድልህ

አዝ:- ንቃ ፡ ክርስቲያን ፡ ንቃ
በሐሰት ፡ ነቢያት ፡ አትዘናጋ (፪x)

ትክክለኛ ፡ ነቢዮች ፡ አሉ
የጌታን ፡ ብቻ ፡ የሚናገሩ
እነርሱንማ ፡ መች ፡ ሊሰሟቸው
ደፍሮ ፡ ይሏቸዋል ፡ ሟርተኛች ፡ ናቸው

አዝ:- ንቃ ፡ ክርስቲያን ፡ ንቃ
በሐሰት ፡ ነቢያት ፡ አትዘናጋ (፪x)