ከወደድኩህ (Kewededkuh) - አዜብ ፡ መለሰ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አዜብ ፡ መለሰ
(Azeb Melesse)

Azeb Melesse 1.jpeg


(1)

የነፍስ ፡ አባቴ
(Yenefs Abatie)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፬ (2011)
ቁጥር (Track):

(2)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአዜብ ፡ መለሰ ፡ አልበሞች
(Albums by Azeb Melesse)

"ፍቅር ፡ ጌታ ፡ ጌታ
ፍቅር ፡ ኢየሱስ ፡ አንተ ፡ ብቻ
አንተ ፡ ብቻ"

አዝ:- ከወደድኩህ ፡ የእውነቴን ፡ የእውነቴን ፡ ልውደድህ
ካፈቀርኩህ ፡ የእውነቴን ፡ የእውነቴን ፡ ላፍቅርህ
ቃሌ ፡ ሌላ ፡ ተግባር ፡ ሌላ ፡ አይሁንብህ

የአንተ ፡ ፍቅር ፡ እንከን ፡ የሌለበት
አሳልፎ ፡ ነፍስን ፡ እስከ ፡ መስጠት
ከዚህ ፡ ዕውቀት ፡ መማር ፡ እንኳን ፡ ባልችል
እኔ ፡ አፍቅሬ ፡ አይቻለሁ ፡ በምድር

አዝ:- ከወደድኩህ ፡ የእውነቴን ፡ የእውነቴን ፡ ልውደድህ
ካፈቀርኩህ ፡ የእውነቴን ፡ የእውነቴን ፡ ላፍቅርህ
ቃሌ ፡ ሌላ ፡ ተግባር ፡ ሌላ ፡ አይሁንብህ

ሰው ፡ ስጥተኀኝ ፡ ወድጄ ፡ ከልቤ
ስገልጥለት ፡ ፍቅሬን ፡ በስራዬ
ሚከፈለውን ፡ ዋጋ ፡ ከፍያለሁ
በሕይወቴ ፡ ብዙ ፡ አሳልፊያለሁ

አዝ:- ከወደድኩህ ፡ የእውነቴን ፡ የእውነቴን ፡ ልውደድህ
ካፈቀርኩህ ፡ የእውነቴን ፡ የእውነቴን ፡ ላፍቅርህ
ቃሌ ፡ ሌላ ፡ ተግባር ፡ ሌላ ፡ አይሁንብህ

ፍቅር ፡ ማለት ፡ እራስን ፡ መስጠት ፡ ነው
ለወደዱት ፡ ታማኝ ፡ መሆን
ለአንተ ፡ ያለኝን ፡ ፍቅር ፡ ስፈትሸው
ወድሃለሁ ፡ ምለው ፡ ውሸቴን ፡ ነው

አዝ:- ከወደድኩህ ፡ የእውነቴን ፡ የእውነቴን ፡ ልውደድህ
ካፈቀርኩህ ፡ የእውነቴን ፡ የእውነቴን ፡ ላፍቅርህ
ቃሌ ፡ ሌላ ፡ ተግባር ፡ ሌላ ፡ አይሁንብህ

ምላሽ ፡ መስጠት ፡ ለአንተ ፡ ለፍቅርህ ፡ ሚሆን
ከወደድከኝ ፡ ጌታ ፡ ላቅርብልህ ፡ ምላሽ

አንደበቴ ፡ በጣም ፡ እንደምወድህ
ቢመሰክር ፡ ውዴ ፡ ማሬ ፡ ብልህ
ምን ፡ ይጠቅማል ፡ ቃላት ፡ ብደረድር
ተግባር ፡ የለሽ ፡ ከሆነ ፡ የኔ ፡ ፍቅር

አዝ:- ከኖርኩልህ ፡ የእውነቴን ፡ የእውነቴን ፡ ልኑርልህ
ከመሰልኩህ ፡ የእውነቴን ፡ የእውነቴን ፡ ልምሰልህ
ቃሌ ፡ ሌላ ፡ ተግባር ፡ ሌላ ፡ አይሁንብህ

ከአፌ ፡ የሚወጣው ፡ ክሽን ፡ ያለ ፡ ያማረ
ስራዬ ፡ የዓለም ፡ ድኖ ፡ እንዳልዳነ
የእውነት ፡ ብወድህ ፡ ይሄ ፡ ይለውጠኛል
ቃሌን ፡ ከተግባሬ ፡ አንድ ፡ አድርግልኝ

አዝ:- ከኖርኩልህ ፡ የእውነቴን ፡ የእውነቴን ፡ ልኑርልህ
ከመሰልኩህ ፡ የእውነቴን ፡ የእውነቴን ፡ ልምሰልህ
ቃሌ ፡ ሌላ ፡ ተግባር ፡ ሌላ ፡ አይሁንብህ

አንተ ፡ ትቀጣለህ ፡ ሃይለኛ ፡ ነህ ፡ ብዬ
እሳት ፡ እንዳልጣል ፡ ሲኦልን ፡ ፈርቼ
ይህን ፡ አልፈልግም ፡ ባፈቅርህ ፡ በቂ ፡ ነው
ላፈቀሩት ፡ መኖር ፡ አይከብድም ፡ ቀላል ፡ ነው

አዝ:- ከኖርኩልህ ፡ የእውነቴን ፡ የእውነቴን ፡ ልኑርልህ
ከመሰልኩህ ፡ የእውነቴን ፡ የእውነቴን ፡ ልምሰልህ
ቃሌ ፡ ሌላ ፡ ተግባር ፡ ሌላ ፡ አይሁንብህ

የምትወደኝ ፡ ጌታ ፡ በዘለዓለም ፡ ፍቅርህ
አንዴ ፡ ወደኀኛል ፡ በዘለዓለም ፡ ፍቅርህ
ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ የልቤ ፡ ወዳጅ ፡ ነህ
የነፍሴ ፡ ወዳጅ ፡ ነህ