From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
አዝ:- ከሁኔታ ፡ በላይ ፡ ጌታ ፡ የበላይ (፪x) (ጌታ ፡ የበላይ (፪x))
ከእኔ ፡ ችግር ፡ በላይ ፡ ጌታ ፡ የበላይ (፪x) (ጌታ ፡ የበላይ (፪x))
ብዙ ፡ ጥያቄ ፡ እንቆቅልሽ ፡ እያለኝ
ግን ፡ እዘምራለሁ ፡ ሁሌ ፡ ደስተኛ ፡ ነኝ
ለእኔ ፡ የተከፈለው ፡ ትልቅ ፡ የደም ፡ ዋጋ
አይመጣጠንም ፡ ከሁኔታዬ ፡ ጋር
አዝ:- እንቆቅልሼ ፡ እያለ
ችግር ፡ መከራ ፡ እያለ
ግን ፡ እዘምራለሁ ፡ ድል ፡ አለ
ግን ፡ እዘምራለሁ ፡ መልስ ፡ አለ (፪x)
ከሁኔታ ፡ በላይ ፡ ጌታ ፡ የበላይ (፪x) (ጌታ ፡ የበላይ (፪x))
ከእኔ ፡ ችግር ፡ በላይ ፡ ጌታ ፡ የበላይ (፪x) (ጌታ ፡ የበላይ (፪x))
በእንግድነት ፡ አገር ፡ ለጊዜው ፡ ምኖረው
በምታልፈው ፡ ዓለም ፡ ትቼው ፡ ለምሄደው
ቢሞላ ፡ ባይሞላ ፡ እኔ ፡ ምን ፡ ቸገረኝ
ስሄድ ፡ ምገባበት ፡ በሰማይ ፡ ቤት ፡ አለኝ
አዝ:- እንቆቅልሼ ፡ እያለ
ችግር ፡ መከራ ፡ እያለ
ግን ፡ እዘምራለሁ ፡ ድል ፡ አለ
ግን ፡ እዘምራለሁ ፡ መልስ ፡ አለ (፪x)
ከሁኔታ ፡ በላይ ፡ ጌታ ፡ የበላይ (፪x) (ጌታ ፡ የበላይ (፪x))
ከእኔ ፡ ችግር ፡ በላይ ፡ ጌታ ፡ የበላይ (፪x) (ጌታ ፡ የበላይ (፪x))
እንዳላጉረመርም ፡ አፌን ፡ በምሥጋና
ሃዘንተኛ ፡ እንዳልመስል ፡ ፊቴ ፡ እያበራ
ኢሄ ፡ እንዴት ፡ ሆነ ፡ ለምትጠይቁኝ
ሁሉን ፡ የሚያስረሳ ፡ አባት ፡ ስላለኝ
አዝ:- እንቆቅልሼ ፡ እያለ
ችግር ፡ መከራ ፡ እያለ
ግን ፡ እዘምራለሁ ፡ ድል ፡ አለ
ግን ፡ እዘምራለሁ ፡ መልስ ፡ አለ (፪x)
ከሁኔታ ፡ በላይ ፡ ጌታ ፡ የበላይ (፪x) (ጌታ ፡ የበላይ (፪x))
ከእኔ ፡ ችግር ፡ በላይ ፡ ጌታ ፡ የበላይ (፪x) (ጌታ ፡ የበላይ (፪x))
|