እዩልኛ (Eyulegna) - አዜብ ፡ መለሰ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አዜብ ፡ መለሰ
(Azeb Melesse)

Azeb Melesse 1.jpeg


(1)

የነፍስ ፡ አባቴ
(Yenefs Abatie)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፬ (2011)
ቁጥር (Track):

(1)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአዜብ ፡ መለሰ ፡ አልበሞች
(Albums by Azeb Melesse)

 
አዝ:- ምን ፡ ነካት ፡ ምን ፡ ነካት ፡ ምን ፡ ሆነች ፡ አትበሉ
ባይሆን ፡ የነካኝን ፡ ኢየሱሴን ፡ እዩ
እዩልኛ ፡ እንዲህ ፡ ያዘመረኝ ፡ እኔን ፡ የኢየሱሴን ፡ ስራ
እዩልኛ ፡ አደናንቁልኛ
እዩልኛ ፡ አንዲህ ፡ ያስጨፈረኝ ፡ እኔን ፡ የኢየሱሴን ፡ ስራ
እዩልኛ ፡ አደናንቁልኛ ፣ እዩልኛ

ነፍሴን ፡ ለታደጋት ፡ ባለውለታዬ
አውልቆ ፡ ለጣለው ፡ እድፋሙን ፡ ልብሴን
ብንከባለልለት ፡ በሰበብ ፡ ባስባቡ
ምን ፡ ነካት ፡ ያላቹህ ፡ እኔን ፡ አትታዘቡ
ገና ፡ ገና ፡ አመልካለሁ ፣ ገና ፡ ገና ፡ እዘምራለሁ
ገና ፡ ገና ፡ እሰግዳለሁ ፣ ገና ፡ ገና ፡ እዘላለሁ

አዝ:- ምን ፡ ነካት ፡ ምን ፡ ነካት ፡ ምን ፡ ሆነች ፡ አትበሉ
ባይሆን ፡ የነካኝን ፡ ኢየሱሴን ፡ እዩ
እዩልኛ ፡ እንዲህ ፡ ያዘመረኝ ፡ እኔን ፡ የኢየሱሴን ፡ ስራ
እዩልኛ ፡ አደናንቁልኛ
እዩልኛ ፡ አንዲህ ፡ ያስጨፈረኝ ፡ እኔን ፡ የኢየሱሴን ፡ ስራ
እዩልኛ ፡ አደናንቁልኛ ፣ እዩልኛ

ስላልጠገበች ፡ ነው ፡ የዓለም ፡ ነገር
እግዚአብሔር ፡ ቤት ፡ መጥታ ፡ እንዲህ ፡ ምትጨፍር
አትበሉ ፡ የልጅ ፡ ነገር ፡ በቃ ፡ ቆርጦልኛል
አሁን ፡ የሚያዘልልለኝ ፡ ሌላ ፡ እውነት ፡ ገብቶኛል
ገና ፡ ገና ፡ አመልካለሁ ፣ ገና ፡ ገና ፡ እዘምራለሁ
ገና ፡ ገና ፡ እሰግዳለሁ ፣ ገና ፡ ገና ፡ እዘላለሁ

አዝ:- ምን ፡ ነካት ፡ ምን ፡ ነካት ፡ ምን ፡ ሆነች ፡ አትበሉ
ባይሆን ፡ የነካኝን ፡ ኢየሱሴን ፡ እዩ
እዩልኛ ፡ እንዲህ ፡ ያዘመረኝ ፡ እኔን ፡ የኢየሱሴን ፡ ስራ
እዩልኛ ፡ አደናንቁልኛ
እዩልኛ ፡ አንዲህ ፡ ያስጨፈረኝ ፡ እኔን ፡ የኢየሱሴን ፡ ስራ
እዩልኛ ፡ አደናንቁልኛ ፣ እዩልኛ

በዉበት ፡ በመንፈስ ፡ ከሆነ ፡ ከውስጤ
እረፊ ፡ አትበሉኝ ፡ ላምልክ ፡ እንደልቤ
ከዚም ፡ በላይ ፡ ካለ ፡ ምናለ ፡ ባደርገው
የተሰራልኝን ፡ እኔ ፡ ነኝ ፡ የማውቀው
ገና ፡ ገና ፡ አመልካለሁ ፣ ገና ፡ ገና ፡ እዘምራለሁ
ገና ፡ ገና ፡ እሰግዳለሁ ፣ ገና ፡ ገና ፡ እዘላለሁ

አዝ:- ምን ፡ ነካት ፡ ምን ፡ ነካት ፡ ምን ፡ ሆነች ፡ አትበሉ
ባይሆን ፡ የነካኝን ፡ ኢየሱሴን ፡ እዩ
እዩልኛ ፡ እንዲህ ፡ ያዘመረኝ ፡ እኔን ፡ የኢየሱሴን ፡ ስራ
እዩልኛ ፡ አደናንቁልኛ
እዩልኛ ፡ አንዲህ ፡ ያስጨፈረኝ ፡ እኔን ፡ የኢየሱሴን ፡ ስራ
እዩልኛ ፡ አደናንቁልኛ ፣ እዩልኛ

በአይምሮዬ ፡ ብሆን ፡ እኔስ ፡ ለሰው???
????? ፡ ለአምላኬ ፡ ትልቅ ፡ ለሆነው
አቀርብለታለሁ ፡ መስዋዕቴን ፡ በሙሉ
መቼም ፡ ዝም ፡ አልልም ፡ ምድር ፡ ፍጥረት ፡ ስሙ
ገና ፡ ገና ፡ አመልካለሁ ፣ ገና ፡ ገና ፡ እዘምራለሁ
ገና ፡ ገና ፡ እሰግዳለሁ ፣ ገና ፡ ገና ፡ እዘላለሁ

ገና ፡ እዘላለሁ ፡ ገና ፣ ገና ፡ እሰግዳለሁ ፡ ገና
ኢየሱሴ ፡ ለታደገኝ ፡ ለጌታዬ ፣ ገና ፡ እዘላለሁ ፡ ገና
ገና ፡ ገና (፬x) ፡ ገና ፡ ገና (፬x) ፡ (ገና ፡ እሰግዳለሁ ፡ ገና)