እውነት ፡ ነው (Ewnet New) - አዜብ ፡ መለሰ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አዜብ ፡ መለሰ
(Azeb Melesse)

Azeb Melesse 1.jpeg

(1)

የነፍስ ፡ አባቴ
(Yenefs Abatie)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፬ (2011)
ቁጥር (Track):

(9)

ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአዜብ ፡ መለሰ ፡ አልበሞች
(Albums by Azeb Melesse)

አዝ:- ዓለም ፡ ከሚሰጣችሁ ፡ ደስታ
እኔ ፡ ምሰጣቹህ ፡ ይበልጣል ፡ ያልከው ፡ እውነት ፡ ነው (፫x)
ዓለም ፡ ከሚሰጣችሁ ፡ ሰላም
እኔ ፡ ምሰጣቹህ ፡ ይበልጣል ፡ ያልከው ፡ እውነት ፡ ነው (፫x)

የዓለምን ፡ ደስታ ፡ እናሳይሽ ፡ ቢሉኝ
እኔም ፡ ተስማምቼ ፡ ተነስቼ ፡ ሄድኩኝ
የሙዚቃው ፡ ጩኀት ፡ ጭፈራ ፡ ዘፈኑ
ለዐይን ፡ የሚስበው ፡ የመብራት ፡ ድምቀቱ
ቅልጥ ፡ ካለው ፡ መንደር ፡ እግሬ ፡ እንደወጣ
ብፈልግ ፡ አጣሁት ፡ የነበረው ፡ ደስታ

አወይ ፡ አወይ ፡ የዓለም ፡ ደስታ
ብልጭ ፡ ብሎ ፡ ወዲያው ፡ የሚጠፋ
ቋሚ ፡ የሆነ ፡ ደስታ ፡ የሚገኘው
ከእግዚአብሔር ፡ ከእርሱ ፡ ብቻ ፡ ነው
አወይ ፡ አወይ ፡ የዓለም ፡ ደስታ
በኖ ፡ የሚያልቅ ፡ ልክ ፡ እንደጤዛ
እውነተኛ ፡ የውስጥ ፡ ሰላሜ
እንደ ፡ ኢየሱስ ፡ ማን ፡ አለ ፡ ለእኔ

አዝ:- ዓለም ፡ ከሚሰጣችሁ ፡ ደስታ
እኔ ፡ ምሰጣቹህ ፡ ይበልጣል ፡ ያልከው ፡ እውነት ፡ ነው (፫x)
ዓለም ፡ ከሚሰጣችሁ ፡ ሰላም
እኔ ፡ ምሰጣቹህ ፡ ይበልጣል ፡ ያልከው ፡ እውነት ፡ ነው (፫x)

ክቡሩን ፡ ሰው ፡ አየሁ ፡ እራሱን ፡ ሲጥል
ትንሹ ፡ ትልቁ ፡ በወይን ፡ ጠጅ ፡ ሲሰክር
እርግጥ ፡ ነው ፡ ለጊዜው ፡ ደስታንም ፡ ይሰጣል
ማታ ፡ ላይ ፡ አስቆ ፡ ጠዋት ፡ ያስለቅሳል
እኔ ፡ ስላየሁኝ ፡ እመሰክራለሁ
የደስታው ፡ ምንጭ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ነው

ሁሉም ፡ ነገር ፡ ቢተርፍ ፡ ቢበዛ
እንደ ፡ ልብህ ፡ ብትሆን ፡ እንደ ፡ አሻህ
የሰላሙን ፡ ንጉሥ ፡ አለቃ
ካላገኘህ ፡ መቼም ፡ አትረካ
እግዚአብሔር ፡ ጋር ፡ ፍፁም ፡ የሆነ
ማይወሰድ ፡ ሰላም ፡ እያለ
አትባክን ፡ አትድከም ፡ ይብቃህ
እርፍ ፡ በል ፡ አይ ፡ ኢየሱስ ፡ ጋር

አዝ:- ዓለም ፡ ከሚሰጣችሁ ፡ ደስታ
እኔ ፡ ምሰጣቹህ ፡ ይበልጣል ፡ ያልከው ፡ እውነት ፡ ነው (፫x)
ዓለም ፡ ከሚሰጣችሁ ፡ ሰላም
እኔ ፡ ምሰጣቹህ ፡ ይበልጣል ፡ ያልከው ፡ እውነት ፡ ነው (፫x)

አንዱ ፡ ለመደሰት ፡ ሲደክም ፡ ሲለፋ
ሌላው ፡ ሰላም ፡ አጥቶ ፡ እራሱን ፡ ሲያጠፋ
ዓለም ፡ ልትሰጠኝ ፡ የማትችለው ፡ ሃብቴ
ከላይ ፡ ያገኘሁት ፡ ትልቁ ፡ ንብረቴ
ምንም ፡ ነገር ፡ ሳይኖር ፡ እኔ ፡ ጋር ፡ ያለው ፡ እርካታ
አሜን ፡ ያስብለኛል ፡ እንኳን ፡ ሆንኩ ፡ የጌታ

ብርና ፡ ወርቅ ፡ የማይተካው
ሚበልጥ ፡ ነው ፡ እኔ/አንተ ፡ ጋር ፡ ያለው
አቤት ፡ እኔ ፡ እድለኛ ፡ ነኝ/ክርስትያን ፡ እድለኛ ፡ ነህ
የሚያሳርፍ ፡ አምላክ ፡ ነው ፡ ያለኝ (፪x)

አዝ:- ዓለም ፡ ከሚሰጣችሁ ፡ ደስታ
እኔ ፡ ምሰጣቹህ ፡ ይበልጣል ፡ ያልከው ፡ እውነት ፡ ነው (፫x)
ዓለም ፡ ከሚሰጣችሁ ፡ ሰላም
እኔ ፡ ምሰጣቹህ ፡ ይበልጣል ፡ ያልከው ፡ እውነት ፡ ነው (፫x)