From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ኢትዮጵያ (፬x)
ስንጮህ ፡ ስናለቅስ ፡ ሳይሰማው ፡ ቀርቶ
አይደል ፡ ላለማገዝ ፡ ላለመርዳት ፡ ብሎ
አሁን ፡ ምናየውን ፡ ዳግም ፡ እንዳናየው
እስከመጨረሻ ፡ ሊቀብረን ፡ ሊያስቀረን
አዝ:- ኢትዮጵያ ፡ መከራሽ ፡ እንደዚህ ፡ የበዛው
ጨለማው ፡ እንዲህ ፡ የበረታው
የኢየሱሴ ፡ ስራ ፡ ይገለጥ ፡ ዘንድ ፡ ነው
ስለ ፡ እግዚአብሔር ፡ ክብር ፡ ነው ፡ እንጂ
ልትጠፊ ፡ አይደለም ፡ ልትዋረጂ
ኢትዮጵያ (፬x)
ዛሬ ፡ የሚቀመስ ፡ ምንም ፡ ነገር ፡ ሳይኖር
ነገ ፡ ይጠገባል ፡ ተርፎ ፡ ይሸጣል ፡ ቢለን
የችግሩ ፡ ብዛት ፡ ግራ ፡ ቢያጋባንም
ቃል ፡ ወጥቷል ፡ ከሰማይ ፡ መሆኑ ፡ አይቀርም
አዝ:- ኢትዮጵያ ፡ መከራሽ ፡ እንደዚህ ፡ የበዛው
ጨለማው ፡ እንዲህ ፡ የበረታው
የኢየሱሴ ፡ ስራ ፡ ይገለጥ ፡ ዘንድ ፡ ነው
ስለ ፡ እግዚአብሔር ፡ ክብር ፡ ነው ፡ እንጂ
ልትጠፊ ፡ አይደለም ፡ ልትዋረጂ
ሰው ፡ ደመናን ፡ አይቶ ፡ ሊዘንብ ፡ ነው ፡ ይላል
አምላኬ ፡ በራሱ ፡ ተማምኖ ፡ ያወራል
ተስፋ ፡ ገብቶላታል ፡ ላለሁባት ፡ ምድሬ
እኔ ፡ እርግጠኛ ፡ ነኝ ፡ ታየዋልች ፡ ህልሜን
አዝ:- ኢትዮጵያ ፡ መከራሽ ፡ እንደዚህ ፡ የበዛው
ጨለማው ፡ እንዲህ ፡ የበረታው
የኢየሱሴ ፡ ስራ ፡ ይገለጥ ፡ ዘንድ ፡ ነው
ስለ ፡ እግዚአብሔር ፡ ክብር ፡ ነው ፡ እንጂ
ልትጠፊ ፡ አይደለም ፡ ልትዋረጂ
የኢትዮጵያን ፡ መባረክ ፡ አትጠራጠሩ
ይሄ ፡ በተአምር ፡ አይሆንም ፡ አትበሉ
እግዚአብሔር ፡ አለ ፡ ሆነ ፡ ነው ፡ በቃሉ
እርሱ ፡ እውነተኛ ፡ አይዋሽም ፡ እመኑ
አዝ:- ኢትዮጵያ ፡ መከራሽ ፡ እንደዚህ ፡ የበዛው
ጨለማው ፡ እንዲህ ፡ የበረታው
የኢየሱሴ ፡ ስራ ፡ ይገለጥ ፡ ዘንድ ፡ ነው
ስለ ፡ እግዚአብሔር ፡ ክብር ፡ ነው ፡ እንጂ
ልትጠፊ ፡ አይደለም ፡ ልትዋረጂ
ኢትዮጵያ (፬x)
|