From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
አዝ:- ብዙዎች ፡ እንደፈለጋቸው
አንተንም ፡ ሳይፈሩ ፡ የሚኖሩ ፡ ናቸው
ሲላቸው ፡ እንደምኞታቸው ፡ ቃልህን ፡ ይገልጻሉ
እራሳቸው ፡ ስተው ፡ ሌላውን ፡ ያስታሉ
አሉ ፡ ደግሞ ፡ ጥቂት ፡ አንተን ፡ የሚፈሩ
ምህረትህን ፡ ታምነው ፡ በጽድቅ ፡ የሚኖሩ
ታጋሽ ፡ ቸር ፡ ሩህሩህ ፡ ምህረትህ ፡ የበዛ
ለእነሱ ፡ ደግ ፡ ነህ ፡ ጨካኝ ፡ ከተቆጣ
እኔ ፡ ከእነዚህ ፡ ጋር ፡ ፈጥኜ ፡ እስማማለሁ
ላለፈው ፡ በደሌ ፡ ንስሃ ፡ እገባለሁ
ድንገት ፡ ሳትጥለኝ ፡ ዛሬ ፡ እመለሳለሁ
እመለሳለሁ ፡ ፍሬም ፡ ማያፈራ ፡ የደረቀ ፡ እንጨት
ማይጠቅም ፡ ዛፍ ፡ ተቆርጦ ፡ መጣል ፡ ነው ፡ በማይጠፋው ፡ እሳት
ልትመጣ ፡ ነው ፡ ክብርህን ፡ ልትገልጥ ፡ ቤትህን ፡ ልታጠራ
ኀጢአት ፡ ልትቀጥፍ ፡ ጅራፍህን ፡ ይዘህ ፡ ተነስተሃልና
አይሆንም ፡ ብሎ ፡ ማነው ፡ ባለስልጣን ፡ የሚከለክልህ
እንዴ ፡ ከያዝከኝ ፡ የትኛው ፡ ብርቱ ፡ ነው ፡ ከእጅህ ፡ የሚያስጥለኝ
እመለሳለሁ ፡ የኔ ፡ መጨረሻ ፡ የኔ ፡ እድል ፡ ፈንታዬ
እመለሳለሁ ፡ እንደ ፡ እንጨቱ ፡ እንዳይሆን ፡ መልሰኝ ፡ ጌታዬ
መልሰኝ ፡ ጌታዬ ፡ መልሰኝ
አዝ:- ብዙዎች ፡ እንደፈለጋቸው
አንተንም ፡ ሳይፈሩ ፡ የሚኖሩ ፡ ናቸው
ሲላቸው ፡ እንደምኞታቸው ፡ ቃልህን ፡ ይገልጻሉ/ይጠቅሳሉ
እራሳቸው ፡ ስተው ፡ ሌላውን ፡ ያስታሉ (፬x)
|