ቤት ፡ አለኝ (Biet Alegn) - አዜብ ፡ መለሰ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
አዜብ ፡ መለሰ
(Azeb Melesse)

Azeb Melesse 1.jpeg


(1)

የነፍስ ፡ አባቴ
(Yenefs Abatie)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፬ (2011)
ቁጥር (Track):

(8)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአዜብ ፡ መለሰ ፡ አልበሞች
(Albums by Azeb Melesse)

 
ቤት ፡ አለኝ ፡ ቤት ፡ አለኝ ፡ ቤት (፪x)
ስገባበት ፡ ኦሆ ፡ እርፍ ፡ ምልበት
በሰማይ ፡ አለኝ ፡ ቤት

አዝ:- የሰማዩን ፡ ቤቴን ፡ ሳስበው
ይገርመኛል ፡ እደነቃለሁ
እንደምድሩ ፡ አላፊ ፡ አይደለ
ጸንቶ ፡ ሚኖር ፡ እጅግ ፡ ያማረ

የሰው ፡ እጅ ፡ ጭራሽ ፡ ያልነካው
ከአይምሮ ፡ በላይ ፡ የሆነው
አምላኬ ፡ እራሱ ፡ የገነባው
የምድር ፡ ሃብት ፡ ቢከማች ፡ የማይተካው

አዝ:- የሰማዩን ፡ ቤቴን ፡ ሳስበው
ይገርመኛል ፡ እደነቃለሁ
እንደምድሩ ፡ አላፊ ፡ አይደለ
ጸንቶ ፡ ሚኖር ፡ እጅግ ፡ ያማረ

ችግርን ፡ የማላይበት
ሃዘን ፡ ለቅሶ ፡ ከቶ ፡ የሌለበት
አምላኬ ፡ ሚመለክበት
ዘለዓለም ፡ እኔም ፡ ማርፍበት

አዝ:- የሰማዩን ፡ ቤቴን ፡ ሳስበው
ይገርመኛል ፡ እደነቃለሁ
እንደምድሩ ፡ አላፊ ፡ አይደለ
ጸንቶ ፡ ሚኖር ፡ እጅግ ፡ ያማረ

ምንኛ ፡ እድለኛ ፡ ነኝ
የእግዚአብሔር ፡ መንግሥት ፡ ወራሽ ፡ ነኝ
አልሰጋም ፡ ምን ፡ እሆን ፡ ብዬ
ዋስትና ፡ ስላለኝ ፡ ብዬ

አዝ:- የሰማዩን ፡ ቤቴን ፡ ሳስበው
ይገርመኛል ፡ እደነቃለሁ
እንደምድሩ ፡ አላፊ ፡ አይደለ
ጸንቶ ፡ ሚኖር ፡ እጅግ ፡ ያማረ

ና ፡ ኢየሱስዬ ፡ ናልኝ
ና ፡ ኢየሱስዬ ፡ ና ፡ ናልኝ
በጣም ፡ ናፈቅከኝ ፡ እጅግ ፡ ናፈቅከኝ
በጣም ፡ ናፈቅከኝ ፡ እጅግ ፡ ናፈቅከኝ (፪x)
በጣም ፡ ናፈቅከኝ ፡ እጅግ ፡ ናፈቅከኝ (፪x)