የነፍሴ ፡ መድኃኒት (Yenefse Medhanit) - አዜብ ፡ ኃይሉ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
አዜብ ፡ ኃይሉ
(Azeb Hailu)

Lyrics.jpg


(6)

ሕያው ፡ አምላክ ፡ ነህ
(Hiyaw Amlak Neh)

ዓ.ም. (Year): 2024
ቁጥር (Track):

(1)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአዜብ ፡ ኃይሉ ፡ አልበሞች
(Albums by Azeb Hailu)

ባንተ ምሕረት
ባንተ ይቅርታ
ነፍሴ እፎይ አለች
አረፈች ጌታ (አረፈች ጌታ)
ሰላም ተሰማኝ
ተፅናናሁኝ (ተፅናናሁኝ)
የኃጢአት እዳዬ ተሽሮልኝ (ተሽሮልኝ)

የነፍሴ መድኃኒት ሆይ
የእግዚአብሔር ልጅ ሆይ
በመስቀል ላይ ያማጥክልኝ
ለብቻህን አይደል ወይ (x2)

ሌላ ማነው ከአንተ በስተቀር
በእኔ ሕይወት ምሕረቱ የሚዘመር
ሌላ ማነው ከአንተ በስተቀር
በእኔ አንደበት ፍቅሩ የሚዘመር

መፍትሄ ጠፍቶ ከሞት መዳኛ (ከሞት መዳኛ)
ሁሉ ደካማ ሁሉ ኃጢአተኛ
ተጨንቀን ሳለን በሞት ፍርሃት (በሞት ፍርሃት)
ኢየሱስ መጣ የአምላክ ምሕረት (የአምላክ ምሕረት)

የነፍሴ መድኃኒት ሆይ
የእግዚአብሔር ልጅ ሆይ
በመስቀል ላይ ያማጥክልኝ
ለብቻህን አይደል ወይ

ሌላ ማነው ከአንተ በስተቀር
በእኔ ሕይወት ምሕረቱ የሚዘመር
ሌላ ማነው ከአንተ በስተቀር
በእኔ አንደበት ፍቅሩ የሚዘመር

ዘምሪ ዘምሪ ነፍሴ ዘምሪ ደስ ይበልሽ
ከዘላለም ሞት መዳኛ መድኃኒት ተወልዶልሽ (2)

በጌታ በኢየሱስ ሞት
ደግሞም በትንሳኤው
ባመንሽ ጊዜ ፈትኖ አደረገሽ ሕያው (2)

የነፍሴ መድኃኒት ሆይ
የእግዚአብሔር ልጅ ሆይ
በመስቀል ላይ ያማጥክልኝ
ለብቻህን አይደል ወይ

ሌላ ማነው ከአንተ በስተቀር
በእኔ ሕይወት ምሕረቱ የሚዘመር
ሌላ ማነው ከአንተ በስተቀር
በእኔ አንደበት ፍቅሩ የሚዘመር