Azeb Hailu/Enetareq/Ante Melkam Neh
< Azeb Hailu | Enetareq
yemitena mezmur new
የሰላም ፡ እንከን ፡ የሌለው አምላኬ ፡ ሁሌም ፡ የሚይስበው ግሩም ፡ ነው ፡ ታማኝነቱ ለዘለዓለም ፡ ቸር ፡ ነው ፡ አቤቱ (፪x)
ሃይልም ፡ የእኔ ፡ ነው ፡ ብርታትም ፡ የእኔ ብለህ ፡ እንዳልከኝ ፡ ደጉ ፡ መድኔ እኔም ፡ አምኜ ፡ ተጠግቼሃለሁ ፡ ክብርህን ፡ አየሁ እኔም ፡ አምኜ ፡ ተጠግቼሃለሁ ፡ ማዳንህን፡ አየሁ
- አዝ፦ አንተ ፡ መልካም ፡ ነህ (፫x)
- የእኔ ፡ ጌታ ፡ አንተ ፡ መልካም ፡ ነህ
- ለእኔ ፡ መልካም ፡ ነህ (፫x)
- ሁልጊዜ ፡ ለእኔ ፡ መልካም ፡ ነህ
አሃሃሃ ፡ የመልካምነትህን ፡ ብዛት አሃሃሃ ፡ የበጐነትህን ፡ ዳር አሃሃሃ ፡ ማንስ ፡ ተናግሮ ፡ አበቃ አሃሃሃ ፡ ማንስ ፡ አቆመ ፡ ከመቁጠር አሃሃሃ ፡ ትላንትም ፡ መልካም ፡ ዛሬም ፡ መልካም አሃሃሃ ፡ ለዘለዓለም ፡ መልካም ፡ ነህ አሀሃህ ፡ አንተን ፡ ወዶ ፡ ክቡር ፡ ጌታ አሃሃሃ ፡ ከማንስ ፡ ጋር ፡ ላስተያይህ
- አዝ፦ አንተ ፡ መልካም ፡ ነህ (፫x)
- የእኔ ፡ ጌታ ፡ አንተ ፡ መልካም ፡ ነህ
- ለእኔ ፡ መልካም ፡ ነህ (፫x)
- ሁልጊዜ ፡ ለእኔ ፡ መልካም ፡ ነህ
</poem> }}