Azeb Hailu/Embi/Temesgen

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search


ጽድቅን እንዲያወራ ምላሴ
እንድትረካ እንድታርፍ ነፍሴ
የዋጀኸኝ አምላኬ መድህኔ
ከዚህች ዓለም አመጻ ኩነኔ


እንዳይረክስ በከንቱ ከንፈሬ
እንዳልጥለው ውድ እንቁውን ክብሬ
ዘመኔን በእጆችህ ያዝክና
አራመድከኝ በሕይወት ጐዳና


አዝ


ተመስገን ተመስገን ተመስገን ልበልህ ደግሜ
ከኃጢአት በሽታ ተፈውሼ ባንተ ታክሜ (፪x)


እንድረዳ ማዳንህን እንዳውቀው
ልቦናዬን ወዳንተ የመለስከው
እንዳያልፈኝ የሕይወቴ መና
ህሊናዬን ለቃልህ አቀናህ


በረከሰው ዓለም የቀደስከኝ
በጽድቅ መንገድ ላይ የመራኸኝ
ከብዙዎች እኔ ተለይቼ
ዘምራለሁ መቅደስህ ገብቼ


አዝ


ተመስገን ተመስገን ተመስገን ልበልህ ደግሜ
ከኃጢአት በሽታ ተፈውሼ ባንተ ታክሜ (፪x)


አልመኝም ከእንግዲህ ወደ ውጪ
ረክቻለሁ ጌታ አንተን መርጬ
የዓለምን ከንቱነት ኮተቷን
ንቄዋለሁ ከነማንነቷ


ወስኛለሁ ልኖር አስከብሬህ
ላፈራልህ ጣፋጭ መልካም ፍሬ
ደስ እንዲልህ ሁሌ በእኔ ጌታ
እገዛለሁ ፈቅጄ በደስታ


አዝ


ተመስገን ተመስገን ተመስገን ልበልህ ደግሜ
ከኃጢአት በሽታ ተፈውሼ ባንተ ታክሜ (፪x)