ንገሩልኝ ፡ መርዶ (Negerulegn Merdo) - አዜብ ፡ ኃይሉ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አዜብ ፡ ኃይሉ
(Azeb Hailu)

Azeb Hailu 1.png


(1)

እምቢ
(Embi)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፭ (2002)
ቁጥር (Track):

(1)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአዜብ ፡ ኃይሉ ፡ አልበሞች
(Albums by Azeb Hailu)

ንገሩልኝ ፡ መርዶ ፡ ለዚያ ፡ ለጠላቴ(፪x)
ወጥመዱ ፡ ተሰብሮ ፡ ማምለጥ ፡ መፈታቴን (፪x)
ዳግም ፡ ላያገኘኝ ፡ ላልገባ ፡ በእጁ (፪x)
እግዚአብሔር ፡ አስቦኝ ፡ አዳነኝ ፡ በልጁ (፪x)

አመለጥኩት ፡ አመለጥኩት ፡ አመለጥኩት
መሃላውን ፡ ቃልኪዳኑን ፡ አፈረስኩት
አዲስ ፡ ኪዳን ፡ አደረግኩኝ ፡ ከኢየሱስ ፡ ጋራ
በጐልጐታ ፡ ቀራንዮ ፡ በዚያ ፡ ተራራ (፪x)

የተተበተበው ፡ ሠንሰለት ፡ አስፈሪው ፡ የሕይወት ፡ ጨለማ
በድንገት ፡ ጠፋ ፡ ገፈፍ ፡ አለ ፡ ከሰማይ ፡ አንድ ፡ ድምጽ ፡ ሰማ
ሲተማመንብኝ ፡ ሲመካ ፡ ሲል ፡ አትወጣም ፡ ፍጹም ፡ ከእጆቼ
የጌታዬ ፡ ፍቅር ፡ ማረከኝ ፡ ወጣሁኝ ፡ ሰይጣንን ፡ ከድቼ

ከሕይወትም ፡ ሕይወት ፡ ከክብርም ፡ ክብር
መውጣት ፡ ከጨለማ ፡ ከሙታን ፡ መንደር
ለሰው ፡ በዘመኑ ፡ ይሄም ፡ አለ ፡ ለካ
መስፈሪያ ፡ የሌው ፡ ሰላም ፡ ከቶ ፡ የማይለካ

ንገሩልኝ ፡ መርዶ ፡ ለዚያ ፡ ለጠላቴ(፪x)
ወጥመዱ ፡ ተሰብሮ ፡ ማምለጥ ፡ መፈታቴን (፪x)
ዳግም ፡ ላያገኘኝ ፡ ላልገባ ፡ በእጁ (፪x)
እግዚአብሔር ፡ አስቦኝ ፡ አዳነኝ ፡ በልጁ (፪x)

አመለጥኩት ፡ አመለጥኩት ፡ አመለጥኩት
መሃላውን ፡ ቃልኪዳኑን ፡ አፈረስኩት
አዲስ ፡ ኪዳን ፡ አደረግኩኝ ፡ ከኢየሱስ ፡ ጋራ
በጐልጐታ ፡ ቀራንዮ ፡ በዚያ ፡ ተራራ (፪x)

ከሰማያት ፡ የተላከውን ፡ የሕይወትን ፡ ጥሪ ፡ ደብዳቤ
ከቶ ፡ እንዳልረዳ ፡ እንዳይገባኝ ፡ እንዳላስተውለው ፡ አንብቤ
ባይኖቼ ፡ ላይ ፡ የተጋረደው ፡ የከበበኝ ፡ ያ ፡ የሞት ፡ ጥላ
በቃሉ ፡ ጉልበት ፡ ተሰበረ ፡ በዙሪያዬ ፡ ብርሃን ፡ ሞላ

መኖርስ ፡ ካልቀረ ፡ ትርጉም ፡ ያለው ፡ ኑሮ
ለዘላለም ፡ ተድላ ፡ ከጌታ ፡ ጋር ፡ አብሮ
አሁን ፡ ገና ፡ ደላኝ ፡ አሁን ፡ ተመቸኝ
ከሁሉ ፡ የበለጠ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ያዘኝ

ንገሩልኝ ፡ መርዶ ፡ ለዚያ ፡ ለጠላቴ(፪x)
ወጥመዱ ፡ ተሰብሮ ፡ ማምለጥ ፡ መፈታቴን (፪x)
ዳግም ፡ ላያገኘኝ ፡ ላልገባ ፡ በእጁ (፪x)
እግዚአብሔር ፡ አስቦኝ ፡ አዳነኝ ፡ በልጁ (፪x)

አመለጥኩት ፡ አመለጥኩት ፡ አመለጥኩት
መሃላውን ፡ ቃልኪዳኑን ፡ አፈረስኩት
አዲስ ፡ ኪዳን ፡ አደረግኩኝ ፡ ከኢየሱስ ፡ ጋራ
በጐልጐታ ፡ ቀራንዮ ፡ በዚያ ፡ ተራራ (፪x)

የክብር ፡ አምላክ ፡ እግዚአብሔር ፡ ወደ ፡ ክብሩ ፡ አስጠግቶኛል
ለዘለዓለም ፡ አይናጋም ፡ ብርቱ ፡ ቅጥር ፡ ሰርቶልኛል
ሺህ ፡ ቢፎክር ፡ ሺህ ፡ ቢዝትብኝ ፡ ጠላቴ ፡ ከየት ፡ ያገኘኛል
የመስቀል ፡ ጀግና ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ከመረቡ ፡ አስመልጦኛል

ደሙ ፡ በጐበኔ ፡ ላይ ፡ ስለተቀባ
የሞት ፡ መላእክተኛ ፡ ከቤቴ ፡ እንዳይገባ
ይህ ፡ ለአምላኬ ፡ ደስታ ፡ መርዶ ፡ ለጠላቴ
ሆኗል ፡ ለዘላለም ፡ (እሰይ) ፡ እኔ ፡ በማምለጤ

ንገሩልኝ ፡ መርዶ ፡ ለዚያ ፡ ለጠላቴ(፪x)
ወጥመዱ ፡ ተሰብሮ ፡ ማምለጥ ፡ መፈታቴን (፪x)
ዳግም ፡ ላያገኘኝ ፡ ላልገባ ፡ በእጁ (፪x)
እግዚአብሔር ፡ አስቦኝ ፡ አዳነኝ ፡ በልጁ (፪x)

አመለጥኩት ፡ አመለጥኩት ፡ አመለጥኩት
መሃላውን ፡ ቃልኪዳኑን ፡ አፈረስኩት
አዲስ ፡ ኪዳን ፡ አደረግኩኝ ፡ ከኢየሱስ ፡ ጋራ
በጐልጐታ ፡ ቀራንዮ ፡ በዚያ ፡ ተራራ (፪x)