Azeb Hailu/Embi/Melas Hulu

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አላደርግም ፡ ለሌላ ፡ ስግደት ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ ፡ አባት (፪x) አልችልም ፡ ለሌላ ፡ መንበርከክ ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ ፡ አምላክ (፪x) አላሰማም ፡ ለሌላ ፡ እልልታ ፡ ላንተ ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ ይህ ፡ ጌታ (፪x) እኔ ፡ አልሰዋም ፡ ለሌላ ፡ አምልኮ ፡ ለሥምህ ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ እኮ (፪x)

አዝ፦ ምላስ ፡ ሁሉ ፡ ያንተን ፡ ክብር ፡ ይናገረው ፡ ያውራ (፪x)
ጉልበት ፡ ሁሉ ፡ ተንበርክኮ ፡ ይደነቅ ፡ በስራህ (፪x)

ባሕር ከፍለህ ሕዝብህን ማሻገርህን የልጆችህን ጠላት በዚያ ማስጠምህን በምድረ በዳው ላይ መናን ማውረድህን ከደረቀው አለት ውሃ ማፍለቅህን

(ኦሆ) ፡ ታምራትህ ፡ (ኦሆ) ፡ ድንቅህን ፡ ሁሉ (ኦሆ) ፡ ይናገረው ፡ (ኦሆ) ፡ ምላስ ፡ ሁሉ (ኦሆ) ፡ ታምራትህን ፡ (ኦሆ) ፡ ድንቅህን ፡ ሁሉ (ኦሆ) ፡ ይዘምረው ፡ (ኦሆ) ፡ ምላስ ፡ ሁሉ

አዝ፦ ምላስ ፡ ሁሉ ፡ ያንተን ፡ ክብር ፡ ይናገረው ፡ ያውራ (፪x)
ጉልበት ፡ ሁሉ ፡ ተንበርክኮ ፡ ይደነቅ ፡ በስራህ (፪x)

የማይፈወሰውን ፡ ደዌ ፡ ማዳንህን የሞተውን ፡ ከመቃብር ፡ ማንሳትህን ሁለት ፡ ዓሣ ፡ ለአምስት ፡ ሺህ ፡ ማጥገብህን በውሃም ፡ ላይ ፡ መሄድ ፡ መጓዝ ፡ መቻልህን

(ኦሆ) ፡ ታምራትህ ፡ (ኦሆ) ፡ ድንቅህን ፡ ሁሉ (ኦሆ) ፡ ይናገረው ፡ (ኦሆ) ፡ ምላስ ፡ ሁሉ (ኦሆ) ፡ ታምራትህን ፡ (ኦሆ) ፡ ድንቅህን ፡ ሁሉ (ኦሆ) ፡ ይዘምረው ፡ (ኦሆ) ፡ ምላስ ፡ ሁሉ

አዝ፦ ምላስ ፡ ሁሉ ፡ ያንተን ፡ ክብር ፡ ይናገረው ፡ ያውራ (፪x)
ጉልበት ፡ ሁሉ ፡ ተንበርክኮ ፡ ይደነቅ ፡ በስራህ (፪x)

ስለ ፡ ሰዎች ፡ ሃጥያት ፡ ራስህን ፡ መስጠትህን በመስቀል ፡ ላይ ፡ ተቸንክረህ ፡ መሞትህን ከሙታንም ፡ በኩር ፡ ሆነህ ፡ መውጣትህን በአባትህ ፡ ቀኝ ፡ ኦ ፡ በክብር ፡ መሆንህን

(ኦሆ) ፡ ታምራትህ ፡ (ኦሆ) ፡ ድንቅህን ፡ ሁሉ (ኦሆ) ፡ ይናገረው ፡ (ኦሆ) ፡ ምላስ ፡ ሁሉ (ኦሆ) ፡ ታምራትህን ፡ (ኦሆ) ፡ ድንቅህን ፡ ሁሉ (ኦሆ) ፡ ይመስክረው ፡ (ኦሆ) ፡ ምላስ ፡ ሁሉ (፪x) </poem> |Audio= }}