Azeb Hailu/Bemejemeria Egziabhier/Eregnaye

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
      እረኛ

|ስለበዛልኝ ምህረቱ ስለደገፈኝ ፀጋው መቋጫ ከቶ አጣሁኝ ሳወራው ቢመሽ ቢነጋ የመልካም ነገር ሁሉ ምንጭ የበጐ ነገር መገኛ የሆነው ጌታ እግዚአብሔር እርሱ ነው የኔ እረኛ (2x)

እረኛዬ የነፍሴ መሰማሪያ እረኛዬ መዋያዬና ማደሪያ እረኛዬ እርሱ ነው የኔ መኖሪያ (፪)

አዝ በምድር ላለው ህይወቴ ከእናቴ ማህፀን ጀምሮ መች ያልቃል የርሱ ቸርነት ተዘርዝሮና ተነግሮ አምላኬ ለኔ ያረገው ባወራው ከቁጥር በዛ ልዘምር እንጂ ሳልሰለች ሳልቆጥበው እንደ ዋዛ

እረኛዬ የነፍሴ መሰማሪያ እረኛዬ መዋያዬና ማደሪያ እረኛዬ እርሱ ነው የኔ መኖሪያ (፪) አዝ

ጀ ሃጥኡ ፀሃይን ሞቆ የአንተን ምስጋና ካወራ ምህረትህን ያየሁ እኔ እኔማ እንዴት አላወራ በልጅህ የአንተ ልጅ ሆኜ ገብቼ ደጅህ ተከፍቶልኝ ያየሁት እና የቀመስኩት የምለው ብዙ ነገር አለኝ


እረኛዬ የነፍሴ መሰማሪያ እረኛዬ መዋያዬና ማደሪያ እረኛዬ እርሱ ነው የኔ መኖሪያ (፪) አዝ

ሙሉ ሆኖ እንደሚፈስ እንደ ውሀ ነው ሰላሜ በክርስቶስ ባገኘሁት የህይወት ቃል ነው መለምለሜ ከማይነጥፍ ከማይደርቀው የህይወት ምንጭ ተጠግቼ የዚህን አለም በረሃ የድርቅ ወሬ መች ፈርቼ


እረኛዬ የነፍሴ መሰማሪያ እረኛዬ መዋያዬና ማደሪያ እረኛዬ እርሱ ነው የኔ መኖሪያ (፪) አዝ