Azeb Hailu/Ashenafi Negn/Mulu Sewenet

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ሙሉ ፡ መስዋዕት ፡ እንከን ፡ የሌለው ፡ ኦሆ
ለአማልክት ፡ አምላክ ፡ ይዣለው ፡ ኢኸው ፡ አሃ
የማያነክስ ፡ ወይ ፡ ያልታወረ ፡ ኦሆ
ለጌቶች ፡ ጌታ ፡ ለተከበረ ፡ አሃ

በፊቱ ፡ የተወደደ ፡ በፊቱ ፡ ከቶ ፡ ያልተናቀ
ሊያሸተው ፡ በአምላኬ ፡ ዘንድ ፡ ዘወትር ፡ የተናፈቀ
ቅዱሱም ፡ ሕያው ፡ መስዋዕት ፡ እራሴ ፡ ነው ፡ ሰውነቴ
ላፍስሰውና ፡ ልሰዋው ፡ ደስ ፡ ይበለው ፡ መድኃኒቴ

አዝ፦ ለአምላኬ ፡ ምሥጋናዬን ፡ እሰዋለሁ
ለንጉሡ ፡ ስዕለቴን ፡ እከፍላለሁ
ይህ ፡ ለእኔ ፡ ሥራዬ ፡ ነው ፡ ልማዴ
በወቅቱ ፡ ክብርን ፡ መስጠት ፡ ለውዴ
ይሄ ፡ ነው ፡ ልማዴ (፫x)

ሙሉ ፡ ለሙም ፡ ጭሶ ፡ የሚቃጠል ፡ ኦሆ
በዙፋኑ ፡ ላይ ፡ እሰይ ፡ የሚያስብል ፡ አሃ
ያለቁጠባ ፡ ያለ ፡ ስስት ፡ ኦሆ
በማደሪያው ፡ ላይ ፡ ይሽተትለት ፡ አሃ

ከነፍሴ ፡ ከፍፁም ፡ ደስታ ፡ የነፍሴ ፡ ነው ፡ ከፍቃዴ
በጠዋትና ፡ በማታ ፡ የምሰዋለት ፡ ለውዴ
የተመረጠውን ፡ መስዋዕት ፡ ከስቡ እና ፡ ከበኩሩ
አምላኬን ፡ ደስ ፡ ካሰኘው ፡ ይኸው ፡ ለዝናው ፡ ለክብሩ

አዝ፦ ለጌታ ፡ ምሥጋናዬን ፡ እሰዋለሁ
ለልዑሉ ፡ ስዕለቴን ፡ እከፍላለሁ
ይህ ፡ ለእኔ ፡ ሥራዬ ፡ ነው ፡ ልማዴ
በወቅቱ ፡ ክብርን ፡ መስጠት ፡ ለውዴ
ይሄ ፡ ነው ፡ ልማዴ (፫x)

የደመናትን ፡ ድንበር ፡ የሚጥስ ፡ ኦሆ
ወደ ፡ ማደሪያው ፡ የሚገሰግስ ፡ አሃ
የተወደደው ፡ ውድ ፡ ምሥጋና ፡ ኦሆ
የተገባው ፡ አምላክ ፡ ነውና ፡ አሃ

በምድር ፡ እስካለሁባት ፡ እስከ ፡ ኖርኩባት ፡ ዘመኔ
የሚገባውን ፡ በሙሉ ፡ አላጓድልም ፡ ከእኔ
በማንኛውም ፡ ሁኔታ ፡ በማንኛውም ፡ ሰዓት
እርሱ ፡ ይቀበለኝ ፡ እንጂ ፡ አልሰለችም ፡ መሰዋት

አዝ፦ ለአምላኬ ፡ ምሥጋናዬን ፡ እሰዋለሁ
ለንጉሡ ፡ ስዕለቴን ፡ እከፍላለሁ
ይህ ፡ ለእኔ ፡ ሥራዬ ፡ ነው ፡ ልማዴ
በወቅቱ ፡ ክብርን ፡ መስጠት ፡ ለውዴ
ይሄ ፡ ነው ፡ ልማዴ (፭x)