ይበሉ (Yibelu) - አይዳ ፡ አብርሃም

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አይዳ ፡ አብርሃም
(Ayda Abraham)

Lyrics.jpg


(2)

የነፍሴ ፡ ሐሴት
(Yenefse Hasset)

ዓ.ም. (Year): 2019
ቁጥር (Track):

(10)

ርዝመት (Len.): 3:55
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአይዳ ፡ አብርሃም ፡ አልበሞች
(Albums by Ayda Abraham)

እስኪ ፡ ይናገሩ ፡ የተሻገርኳቸው ፡ እነዚያ ፡ መንገዶች
ፍቅርና ፡ ምሕረትህ ፡ የደጋገፈኝ ፡ እነዚያ ፡ ቀናቶች
እስኪ ፡ ይናገሩ ፡ የተሻገርኳቸው ፡ እነዚያ ፡ መንገዶች
በእሳት ፡ አምድ ፡ ደመና ፡ ክንድህ ፡ ያሳለፈኝ ፡ እነዚያ ፡ ቀናቶች

ይበሉ
እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ የለም
ይበሉ
እንደ ፡ ጌታ ፡ ያለ ፡ የለም
X፪

ነፍሴ ፡ በእግዚአብሔር ፡ አምናለችና ፡ አታፍርም
አምናለችና ፡ አታፍርም
ትልቅነቱን ፡ ታውቃለችና ፡ አታፍርም
ታውቃለችና ፡ አታፍርም
ይረዳታል ፡ ያግዛታል ፡ ከለላዋም ፡ ሆኖላታል
ይረዳታል ፡ ያግዛታል ፡ ማዳኑንም ፡ ያሳያታል

እላለሁ
እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ የለም
እላለሁ
እንደ ፡ ጌታ ፡ ያለ ፡ የለም
X፪

ሁኔታ ፡ እየመጣ ፡ ሲያነጋግረኝ
ሲያነጋግረኝ
የዛሬውስ ፡ መውጫሽ ፡ ምን ፡ ይሆን ፡ ቢለኝ
ምን ፡ ይሆን ፡ ቢለኝ
X፪

አሄ ፡ እግዚአብሔርን ፡ ይዤ ፡ እኔ ፡ ምን ፡ ሆናለሁ
አሄ ፡ እረድኤቴ ፡ ጋሻ ፡ ሆኖልኝ ፡ እያየሁ
አሄ ፡ እግዚአብሔርን ፡ ይዤ ፡ እኔ ፡ ምን ፡ ሆናለሁ
አሄ ፡ የከፍታዬ ፡ ሰይፍ ፡ ሆኖልኝ ፡ እያየሁ
አሄ ፡ እግዚአብሔርን ፡ ይዤ ፡ እኔ ፡ ምን ፡ ሆናለሁ
አሄ ፡ ነገሬን ፡ በእጆቹ ፡ ይዞልኝ ፡ እያየሁ

እላለሁ
እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ የለም
እላለሁ
እንደ ፡ ጌታ ፡ ያለ ፡ የለም
X፪