From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
እግዚአብሔር ፡ የለም ፡ እንዴት ፡ ትለኛለህ
መኖሩን ፡ ዘወትር ፡ በዙሪያህ ፡ እያየህ
ነፍስህን ፡ ሸጠሃት ፡ ለዓለም ፡ ፍልስፍና
በከንቱ ፡ ሳትለፋ ፡ ወንድሜ ፡ ቶሎ ፡ ና
የፍጥረት ፡ ፈጣሪ ፡ ከመሠረቱ
ቃሉ ፡ ሕያው ፡ ነው ፡ ሁሌም ፡ ክንደ ፡ ብርቱ
የመጀመሪያ ፡ የመጨረሻም ፡ ነው
አልፋና ፡ ኦሜጋ ፡ ሚመስለው ፡ የሌለው
አለ ፡ አለ
እግዚአብሔር ፡ አለ
የዚህች ፡ ዓለም ፡ ሕይወት ፡ ሆኖብን ፡ ብርቱ ፡ ሰልፍ
ከብዶ ፡ ያስጨነቀን ፡ መስሎን ፡ ማይታለፍ
የተደራረበው ፡ የመከራ ፡ ጐርፍም
ተስፋ ፡ አስቆርጦ ፡ የለም ፡ ሊያስብለን
በሁኔታ ፡ አይገመት ፡ በመንገዱ ፡ እጅግ ፡ ጻድቅ
ቃል ፡ የገባውን ፡ አለሁ ፡ ብሎ
ዛሬም ፡ አለ ፡ ሚደርስ ፡ ቶሎ
አለ ፡ አለ
እግዚአብሔር ፡ አለ
ከጥንት ፡ የነበረ ፡ ያለ ፡ የሚኖረው
ሁኔታ ፡ ማይለውጠው ፡ እርሱ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው
ከጥንት ፡ የነበረ ፡ ያለ ፡ የሚኖረው
ልብን ፡ ሚፈውሰው ፡ እርሱ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው
በዘመን ፡ ፍጻሜ ፡ በዓለም ፡ መጨረሻ
ሁሉም ፡ ተደምድሞ ፡ ላይኖር ፡ መመለሻ
በፊቱ ፡ ስንቆም ፡ ሰርቶ ፡ ባኖረን ፡ ፊት
ትርፉ ፡ ጸጸት ፡ እንዳይሆን ፡ አርፍደን ፡ ለጥቂት
ዛሬ ፡ ቀን ፡ ሳለ ፡ ፈጣሪን ፡ እናስብ
የፍቅር ፡ ጥሪውን ፡ ልባችን ፡ ይቀበልው
ለዚህች ፡ አጭር ፡ ሕይወት ፡ ምትጠፋ ፡ እንደ ፡ ጤዛ
ቀን ፡ ሳለ ፡ እንመለስ ፡ አንሞኝ ፡ አንልፋ
አለ ፡ እግዚአብሔር ፡ አለ
አዎ
አለ ፡ እግዚአብሔር ፡ አለ
ታሪክ ፡ ይናገራል ፡ መጸሃፉ
የለም ፡ ያሉት ፡ ሁሉ ፡ እንደጠፉ ፪X
አለ ፡ እግዚአብሔር ፡ አለ
አዎ
አለ ፡ እግዚአብሔር ፡ አለ
|