አለህ ፡ እግዚአብሔር (Aleh Egziabher) - አይዳ ፡ አብርሃም

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አይዳ ፡ አብርሃም
(Ayda Abraham)

Lyrics.jpg


(2)

የነፍሴ ፡ ሐሴት
(Yenefse Hasset)

ዓ.ም. (Year): 2019
ቁጥር (Track):

(7)

ርዝመት (Len.): 5:31
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአይዳ ፡ አብርሃም ፡ አልበሞች
(Albums by Ayda Abraham)

አለህ ፡ አለህ ፡ እግዚአብሔር
አለህ ፡ አንተ ፡ እግዚአብሔር
አለህ ፡ አለህ ፡ እግዚአብሔር
ዛሬም ፡ ሰውን ፡ አልተውክም

አለህ ፡ አለህ ፡ እግዚአብሔር
አለህ ፡ አንተ ፡ እግዚአብሔር
አለህ ፡ አለህ ፡ እግዚአብሔር
ማትንቅ ፡ የሁሉ ፡ ወዳጅ

የአንተ ፡ ፍቅር ፡ በሁሉ ፡ ተፈትኖ
ወቅት ፡ ሳያሸንፈው ፡ ደካማውን ፡ ወዶ
የእናት ፡ ፍቅር ፡ እንኳን ፡ ይለወጥ ፡ ይሆናል
እንደልጅ ፡ አኳኋን ፡ ሁኔታ ፡ ይወሰናል

የማትለዋወጥ ፡ አየን ፡ አንተን ፡ ወዳጅ
እውነተኛ ፡ ወላጅ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ የእኛ ፡ አባት
X፪

አለህ ፡ አለህ ፡ እግዚአብሔር
አለህ ፡ አንተ ፡ እግዚአብሔር
አለህ ፡ አለህ ፡ እግዚአብሔር
ዛሬም ፡ ሰውን ፡ አልተውክም

አለህ ፡ አለህ ፡ እግዚአብሔር
አለህ ፡ አንተ ፡ እግዚአብሔር
አለህ ፡ አለህ ፡ እግዚአብሔር
ማትንቅ ፡ የሁሉ ፡ ወዳጅ

ልጅን ፡ እስከመስጠት ፡ የሚወድ ፡ ፍቅር
የሕይወትን ፡ ትርጉም ፡ አቅጣጫ ፡ ሚቀይር
በዚህ ፡ ማንነትህ ፡ ረስርሳለች ፡ ነፍሴ
ትመሰክራለች ፡ ቀን ፡ ከሌት ፡ አምላኬ

የማትለዋወጥ ፡ አየን ፡ አንተን ፡ ወዳጅ
እውነተኛ ፡ ወላጅ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ የእኛ ፡ አባት
X፪

ከተመስገን ፡ ሌላ ፡ ቃል ፡ አለ ፡ ወይ ፡ ለአንተ ፡ ሚሆንህ
ቃል ፡ አለ ፡ ወይ ፡ ለአንተ ፡ ሚሆንህ
ከተባረክ ፡ ሌላ ፡ ቃል ፡ አለ ፡ ወይ ፡ ለአንተ ፡ ምሰጥህ
ቃል ፡ አለ ፡ ወይ ፡ ለአንተ ፡ ምሰጥህ

ሕይወቴ ፡ በፍቅርህ ፡ ሞልተኸዋልና ፡ ዙፋንህን ፡ ዛሬም ፡ ይክበበው ፡ ምሥጋና
ዘመኔንን ፡ በቃልህ ፡ አስውበሃልና ፡ ዙፋንህን ፡ ዛሬም ፡ ይክበበው ፡ ምሥጋና
X፪