ስላንተ (Selante) - አይዳ ፡ አብርሃም

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አይዳ ፡ አብርሃም
(Ayda Abraham)


(1)

ስላንተ
(Selante)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፯ (2014)
ቁጥር (Track):

(1)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአይዳ ፡ አብርሃም ፡ አልበሞች
(Albums by Ayda Abraham)

ምንድን ፡ ነው ፡ የመኖር ፡ ትርጉሙ ፡ የሕይወት ፡ ጣዕሙ
ምንድን ፡ ነው ፡ ሃብትን ፡ ማካበቱ ፡ ዓለምን ፡ ማትረፉ
ምንድን ፡ ነው ፡ ክብር ፡ ዝና ፡ ማግኘት ፡ ፊደልን ፡ መቁጠሩ
ምንድን ፡ ነው ፡ ውበት ፡ ወጣትነት ፡ ጉብዝናው ፡ ጥቅሙ

አዝ፦ አንተን ፡ ካላከበሩ (፬x)
አንተን ፡ ካላከበሩ (፬x)

ምንድን ፡ ነው ፡ የቃል ፡ ዕውቀት ፡ እድገት ፡ የአገልግሎት ፡ ብዛት
ምንድን ፡ ነው ፡ ቀን ፡ ከሌት ፡ መሮጡ ፡ ሰውን ፡ ለማስደሰት
ምንድን ፡ ነው ፡ በሥጋ ፡ ለባሽ ፡ መከበር ቅዱሱ ፡ መንፈስህ ፡ ሳይኖር
ምንድን ፡ ነው (፫x)

አዝ፦ አንተን ፡ ካላከበሩ (፬x)
አንተን ፡ ካላከበሩ (፬x)

ምንድን ፡ ነው ፡ ስለእኔ ፡ ሳይሆን
ምንድን ፡ ነው ፡ ሕይወቴ ፡ በሙሉ ፡ ካላከበረህ ፡ እንዲሁ
ምንድን ፡ ነው ፡ መድከሚ ፡ ምንድን ፡ ነው ፡ ጥቅሙ
ምንድን ፡ ነው ፡ አላማዬ ፡ ካልሆንከኝ ፡ ኢየሱስ

ከንቱ ፡ ነው (፬x)
ከንቱ ፡ ነው (፬x)

አዝ፦ አንተን ፡ ካላከበሩ (ከንቱ ፡ ነው) (፬x)
አንተን ፡ ካላከበሩ (ከንቱ ፡ ነው) (፬x)