መንፈስ ፡ ቅዱስ (Menfes Qedus) - አይዳ ፡ አብርሃም

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አይዳ ፡ አብርሃም
(Ayda Abraham)

Ayda Abraham 1.jpg


(1)

ስላንተ
(Selante)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፯ (2014)
ቁጥር (Track):

(4)

ርዝመት (Len.): 5:51
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአይዳ ፡ አብርሃም ፡ አልበሞች
(Albums by Ayda Abraham)

መንፈስ ፡ቅዱስ ፡ ከኔ ፡ ጋር ፡ ያለዉ
እርሱ ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ ሚያኮራ ፡ ሌላ ፡ ማን ፡ አለ
መንፈስ ፡ቅዱስ ፡ በውስጤ ፡ ያለዉ
እርሱ ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ ሚያስመካ ፡ ሌላ ፡ ምን ፡ አለ

ሌላ ፡ ምን ፡ አለ ፡ (፬)
ሌላ ፡ ማን ፡ አለ ፡ (፬)

በኃይሌ ፡ አይደለም ፡ ወይም ፡ በብርታቴ ፡
መውጣቴ ፡ መግባቴ ፡ ያማረው ፡ ሕይወቴ
በመንፈሱ ፡ እንጂ ፡ ሁሉን ፡ በሚችለው
ደካማውን ፡ ብርቱ ፡ ብርቱ ፡ በሚያደርገው

አለኝ ፡ እውነቱን ፡ ሚያስተምረኝ
አለኝ ፡ መልካሙን ፡ ሚያሳየኝ
በለመለመ ፡ መስክ ፡ የሚያሳድረኝ
በረፍትም ፡ ዉሃ ፡ ዘንድ ፡ ሁሌ ፡ ሚመራኝ ፡

ያጽናናኛል ፡ ይደግፈኛል ፡
በጐነቱን ፡ ይገልጥልኛል
መካሪዬ ፡ ነው ፡ አለኝታዬ ፡
ዘልቆ ፡ ሚኖር ፡ ውስጤ ፡ ጟዳዬ

አለኝ ፡ እውነቱን ፡ ሚያስተምረኝ
አለኝ ፡ መልካሙን ፡ ሚያሳየኝ
በለመለመ ፡ መስክ ፡ የሚያሳድረኝ
በረፍትም ፡ ዉሃ ፡ ዘንድ ፡ ሁሌ ፡ ሚመራኝ

በቅዱሱ ፡ መንፈስህ ፡ እመካለሁ
በቅዱሱ ፡ መንፈስህ ፡ እኮራለሁ
በቅዱሱ ፡ መንፈስህ ፡ እጽናናለሁ
ከቅዱሱም ፡ መንፈስህም ፡ እማራለሁ

እኮራለሁ ፡ (፬)
እመካለሁ ፡ (፬)