ኢየሱስ (Eyesus) - አይዳ ፡ አብርሃም

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
Broom.png ይህ ፡ ጽሑፍ ፡ ገና ፡ አልተረጋገጠም ። እርማቶች ፡ ሊያስፈልጉት ፡ ይችላል ። ከቻሉ ፡ እርስዎ ፡ ያሻሽሉት
አይዳ ፡ አብርሃም
(Ayda Abraham)

Ayda Abraham 1.jpg


(1)

ስላንተ
(Selante)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፯ (2014)
ቁጥር (Track):

(9)

ርዝመት (Len.): 4:47
ጸሐፊ (Writer): ሰብለ ቲመርጋ
(Seble Timerga
Property "Writer" has been marked for restricted use.
)
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአይዳ ፡ አብርሃም ፡ አልበሞች
(Albums by Ayda Abraham)

ኢየሱስ ከኔ ጋር ነህና አልናወጥም /*3
ኢየሱስ ከኔ ጋር ነህና አልሸበርም/*3

ነገር ግን ልቤን ደስ ይለዋል
ምላሴም ሀሴት ታደርጋለች
ስጋዬም በተስፋ ታድራለች
የታመንኩት ጌታ አቅሜ ነዉ ትላለች

መታመኑን ባንተ ያረገ ሰው ምስጉን ነው* 4
በችሎታህ የተደገፈ ሰው ምስጉን ነው/*4
በሁሉ ላይ ጌታ ነህ
በሁሉ ላይ ንጉስ
በሁሉ ላይ የበላይ
የናዝሬቱ እየሱስ

በፀናው ግንብ በስምህ አመልጣለሁ
በስምህ አመልጣለሁ
በስምህ እሸሸጋለሁ
ከስሞችስ እንደ ስምህ ማነው
በስምህ አመልጣለሁ
በስምህ ከፍ እላለሁ
በሁሉ ላይ ጌታ ነህ
በሁሉ ላይ ንጉስ
በሁሉ ላይ የበላይ
የናዝሬቱ እየሱስ

ጌታ በቀኜ ነህና አልታወክም/*3
ኧረ እኔ አንተ አለኸኝና አልሸበርም/*3
ስለዚህ ልቤን ደስ ይለዋል
ምላሴም ሀሴት ታደርጋለች
ስጋዬም በተስፋህ ታድራለች
የታመንኩት ጌታ አቅሜ ነዉ ትላለች