Awtaru Kebede/Tenestual/Ab Yakeberew
< Awtaru Kebede | Tenestual
ዘማሪ አውታሩ ከበደ ርዕስ አብ ያከበረው አልበም ተነስቷል
በጓዳዬ ሆኜ ቅዱስ ነው ስለው በአደባባይ ላይ ሥራዬን ሰራው ልቤ ቅልጥ አለ በፍቅሩ ትኩሳት ሰላም ነው የሞላው ብትገቡ በእኔ ቤት
አሃሃ ከምድር በታች ከዚያም በላይ እኔ አላየሁም እርሱን መሳይ (፪x) አብ ያከበረ ጌታ እርሱን ብቻ ለውበቱማ የለውም አቻ (፪x)
ዝምታ ሆነ ፀጥታ አካባቢው ላይ ምን መጣ ምትሃት አይደለም ጌታ ነው ማዕበል ወጀቡን ያቆመው (፪x)
ጌታ ነው (፪x) ከሁሉ በላይ ከሁሉ በላይ በሰማይ በምድር የለም የሚታይ የለም የሚታይ
እስቲ ከእርሱ በላይ ማነው የበላይ ማኅተሙን የፈታ ይታወቃል ዎይ እስቲ ከእርሱ በላይ ማነው የበላይ ሞትን ድል የነሳ ይታወቃል ዎይ
አሃሃ ከምድር በታች ከዚያም በላይ እኔ አላየሁም እርሱን መሳይ (፪x) አብ ያከበረ ጌታ እርሱን ብቻ ለውበቱማ የለውም አቻ (፪x)