Awtaru Kebede/Lelitu Nega/Yalegn Yehie New

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ዘማሪ አውታሩ ከበደ ርዕስ ያለኝ ይሄ ነው አልበም ሌሊቱ ነጋ

አምልኬ አልጠግብ አልኩኝ ጌታዬ አንግሼ አልጠግብ አልኩኝ ወዳጄ አጣሁ አጣሁኝ አንተን የሚተካ በምድር በሰማይ አንደኛ ነህ ለካ (፪x)

ምነው ሌላ ቋንቋ ሌላ ሌላ ቋንቋ ቢኖረኝ /ቢፈጠር/ ልብን የሚያረካ (፪x)

አልወጣልህ አለኝ ከልቤ እስቲ ላመስግንህ ጌታዬ ጌታዬ

አዝ ያለኝ ይሄ ነው ያለኝ (፬x)

አጣሁልህ እየሱስ አንተን መሳይ የከበረ በምድር በሰማይ ፍቅርህ ልቤን ጥብቅ አድርጐ ይዞታል እስቲ ዘምር አመስግን ያሰኘኛል

ሥምህ የከበረ የገነነ ነዉ ነዉ ዝናህ የከበረ የገነነ ነዉ ነዉ ጌታ ነህ ጌታ ነህ ከሁሉ በላይ እንዳንተ ያለ በምድር የለም በሰማይ (፪x)

ሰው ያለኝ ይሄ ነው እያለ ሲያወራ የእኔ ግን ጌታ ነው የለውም እኩያ (፪x)

አዝ ያለኝ ጌታ ነው ያለኝ (፪x) ያለኝ እርሱ ነው ያለኝ (፪x)

አምልኬ አልጠግብ አልኩ ጌታዬ አንግሼ አልጠግብህም አልኩ ወዳጄ አጣሁ አጣሁኝ አንተን የሚተካ በምድር በሰማይ አንደኛ ነህ ለካ (፪x)

ምነው ሌላ ቋንቋ ሌላ ሌላ ቋንቋ ቢኖረኝ /ቢፈጠር/ ልብን የሚያረካ (፪x)

አልወጣልህ አለኝ ከልቤ ውለታህ በዛብኝ ጌታዬ ጌታዬ አልወጣልህ አለኝ ከልቤ እስቲ ላመስግንህ ጌታዬ ጌታዬ

አዝ ያለኝ ይሄ ነው ያለኝ (፬x)