Awtaru Kebede/Lelitu Nega/Tsegah Bezto

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ዘማሪ አውታሩ ከበደ ርዕስ ፀጋህ በዝቶ አልበም ሌሊቱ ነጋ

ጨለማው ተገፍፎ ብሩህ ቀን ወጣልኝ ጌታዬ ሃዘኔን ገፈፍ አረገልኝ (፪x) ጨለማው ተገፍፎ ብሩህ ቀን ወጣልኝ ጌታዬ ችግሬን ገፈፍ አረገልኝ (፪x)

ሌላ ሌላማ ሌላ ነገር የለኝም በውስጤ ሌትም ማለዳ ሁሌ ለኔ ብርቅ ነህ ኢየሱሴ

ችላ አላልኩትም የዋልከውን ውለታ ማን ያድነኝ ነበር ሞቶ በኔ ቦታ (፪x) ትዝ ይለኝ ጀመረ ወስጥ ወስጤን መዳኔ ሌላ ተዓምር ባይኖር በቂ ነው ይህ ለኔ (፪x)

አዝ ፀጋህ በዝቶ ከብሬያለሁ ዘመን መጥቶ ታስቤያለሁ (አሃሃ) ምህረትህ በኔ ጸንታ አቆመችኝ ክብር ጌታ አቤት (፭x) ክብር ጌታ (አሃሃ) ክብር ጌታ (አሃሃ) ክብር ጌታ (ሃሌሉያ) ክብር ጌታ (፪x)

ክብር ጌታ (፬x)

ጨለማው ተገፍፎ ብሩህ ቀን ወጣልኝ ጌታዬ ሃዘኔን ገፈፍ አረገልኝ (፪x) ጨለማው ተገፍፎ ብሩህ ቀን ወጣልኝ ጌታዬ ችግሬን ገፈፍ አረገልኝ (፪x)

ሌላ ሌላማ ሌላ ነገር የለኝም በውስጤ ሌትም ማለዳ ሁሌ ለኔ ብርቅ ነህ ኢየሱሴ