Awtaru Kebede/Lelitu Nega/Nuroyien Yetamrat

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ዘማሪ አውታሩ ከበደ

ርዕስ ኑሮዬን የታምራት አልበም ሌሊቱ ነጋ

በላይ በላዩ ላይ በረከት አዞልኛል
አንዱን ሳልጨርሰው ሌላው ይከተለኛል
ገና ሳልፈጽመው የጥያቄዬን ቃል
መልሴ በደጅ ቆሞ በር ያንኳኳልኛል

አዝ ኑሮዬን የታምራት አድርጐታል (፪x)
የኔ እኮ ከሰው ሁሉ ለየት ይላል (፪x)
ትላንትናን አኑሬሃለሁ ዛሬን ደግሞ በታምራቴ
ይልቅስ ተረጋግተህ ኑር ይለኛል ረድዔቴ
ሂድ እንጂ ተረጋግተህ ኑር ይለኛል ረድዔቴ

እረጋጋለሁ አንተ ካልክማ
ልቤ ሰምቶሃል ቃልህን ጌታ (፪x)

ጭንቅ አይለዉም ልቤን ፍርሃት ፍርሃት
ምን በወጣኝ ልፍራ ጌታ ሆኖኝ አባት
የሰማዩ ወፎች ጠግበው ከአደሩ
እንዴት እኔ አልኖርም እነሱ ከኖሩ

አዝ
ኑሮዬን የታምራት አድርጐታል
ኑሮዬን የምስጋና አድርጐታል
የኔ እኮ ከሰው ሁሉ ለየት ይላል (፪x)

ትላንትናን አኑሬሃለሁ ዛሬን ደግሞ በታምራቴ
ይልቅስ ተረጋግተህ ኑር ይለኛል ረድዔቴ
ሂድ እንጂ ተረጋግተህ ኑር ይለኛል ረድዔቴ

እረጋጋለሁ አንተ ካልክማ
ልቤ ሰምቶሃል ቃልህን ጌታ (፪x)

ስለለመድኩኝ ነው የታምራት ኑሮ
ቀርቷል አትበሉኝ ተዓምርማ ድሮ
ተዓምር የፈለገ ወደዚህ ይመልከት
ዝንድሮም ይሰራል ጌታ በኛ ሕይወት

አዝ
ኑሮዬን የታምራት አድርጐታል (፪x)
የኔ እኮ ከሰው ሁሉ ለየት ይላል (፪x)

ትላንትናን አኑሬሃለሁ ዛሬን ደግሞ በታምራቴ
ይልቅስ ተረጋግተህ ኑር ይለኛል ረድዔቴ
ሂድ እንጂ ተረጋግተህ ኑር ይለኛል ረድዔቴ

እረጋጋለሁ አንተ ካልክማ
ልቤ ሰምቶሃል ቃልህን ጌታ (፪x)


እንደዘመርኩት ነው ኑሮዬ
መሠረቴ ሆኗል ጌታዬ
ወጀቡ ቢበዛ ቢያይልም
ቢገፋኝ የሚገፋኝ አልወድቅም (፬x)

እረጋጋለሁ አንተ ካልክማ
ልቤ ሰምቶሃል ቃልህን ጌታ (፪x)