ልቤ ፡ አውቆታል (Lebie Awqotal) - አውታሩ ፡ ከበደ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አውታሩ ፡ ከበደ
(Awtaru Kebede)

Awtaru Kebede 4.jpg


(4)

ሌሊቱ ፡ ነጋ
(Lelitu Nega)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፰ (2005)
ቁጥር (Track):

(8)

ርዝመት (Len.): 5:56
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአውታሩ ፡ ከበደ ፡ አልበሞች
(Albums by Awtaru Kebede)

ስለሆነም ፡ አይደለም ፡ ነገር ፡ ስለተሳካ
ዝም ፡ ብሎ ፡ ደስ ፡ ይለኛል ፡ ልቤ ፡ አውቆታል ፡ ለካ
ስለሆነም ፡ አይደለም ፡ ነገር ፡ ስለተሳካ
በጌታ ፡ ደስ ፡ ይለኛል ፡ ልቤ ፡ አውቆታል ፡ ለካ

ልቤ ፡ አውቆታል ፡ ለካ ፡ ልቤ ፡ አውቆታል ፡ ለካ
መዘመር ፡ አልተውም ፡ ሌሊቱ ፡ ባይነጋ
ልማድ ፡ ሆኖብኛል ፡ ወግ ፡ ወጉን ፡ መናገር
እኔ ፡ እየዘመርኩ ፡ ተከፈተ ፡ ያ ፡ በር

ልቤ ፡ አውቆታል ፡ ለካ ፡ ልቤ ፡ አውቆታል ፡ ለካ
መዘመር ፡ አልተውም ፡ ሌሊቱ ፡ እስኪነጋ
ልማዴ ፡ ይሄ ፡ ነው ፡ ወግ ፡ ወጉን ፡ መናገር
እኔ ፡ እየዘመርኩ ፡ ተከፈተ ፡ ያ ፡ በር

አይችልም ፡ አትበሉኝ ፡ አይችልም ፡ አትበሉኝ
ሳይችል ፡ ይሄን ፡ ጌታ ፡ አይታቹሃል ፡ ወይ
ምስኪኑን ፡ አንስቶት ፡ ቀብቶት ፡ አታዩኝም ፡ ወይ

በተዘጋው ፡ ደጅ ፡ ወስጥ ፡ በተዘራው ፡ ደጅ ፡ ወስጥ
በሩ ፡ ሳይከፈት ፡ ማንስ ፡ ይገባል
ለሰው ፡ የማይቻል ፡ ለእርሱ ፡ ቀላል ፡ ሆኖ ፡ ሙሉ ፡ አይኔ ፡ አይቶታል

ስለሆነም ፡ አይደለም ፡ ነገር ፡ ስለተሳካ
ዝም ፡ ብሎ ፡ ደስ ፡ ይለኛል ፡ ልቤ ፡ አውቆታል ፡ ለካ
ስለሆነም ፡ አይደለም ፡ ነገር ፡ ስለተሳካ
በጌታ ፡ ደስ ፡ ይለኛል ፡ ልቤ ፡ አውቆታል ፡ ለካ

ልቤ ፡ አውቆታል ፡ ለካ (፪x)
መዘመር ፡ አልተውም ፡ ሌሊቱ ፡ ባይነጋ
ልማድ ፡ ሆኖብኛል ፡ ወግ ፡ ወጉን ፡ መናገር
እኔ ፡ እየዘመርኩ ፡ ተከፈተ ፡ ያ ፡ በር

ልቤ ፡ አውቆታል ፡ ለካ (፪x)
መዘመር ፡ አልተውም ፡ ሌሊቱ ፡ እስኪነጋ
ልማዴ ፡ ይሄ ፡ ነው ፡ ወግ ፡ ወጉን ፡ መናገር
እኔ ፡ እየዘመርኩ ፡ ተከፈተ ፡ ያ ፡ በር

ተው ፡ አይችለም ፡ አትበል
ተው ፡ ጌታ ፡ ይችላል ፡ እኮ (፪x)

ተይ ፡ አይችለም ፡ አትበይ
ተይ ፡ ጌታ ፡ ይችላል ፡ እኮ (፪x)

ውልቅ ፡ አድርጌ ፡ ወጣሁት ፡ አልመች ፡ ሲለኝ
እኔ ፡ የለመድኩት ፡ ተዓምር ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ያሳይኝ
አልገዛልህም ፡ አለኝ ፡ ልቤ ፡ ለሌላ
አንበሳና ፡ ድብ ፡ መግደል ፡ ነው ፡ እኮ ፡ የእኔ ፡ ስራ (፪x)

ሰይፌ ፡ አይገባም ፡ ወደ ፡ ሰገባው
ህዝቡን ፡ ያሸበረው ፡ እስቲ ፡ የቱ ፡ ነዉ
የማይወድቅ ፡ ይመስላል ፡ ፊቴ ፡ ተገትሮ
አንዲት ፡ ቃል ፡ በቂ ፡ ነው ፡ ያሳየኛል ፡ ጥሎ (፪x)